ረቡዕ 18 ፌብሩዋሪ 2015

ጭጋጎ

ክረምት ይሉት ወፍራም ምፀት
ይህን ብርድ ብሎ ማለት ዘበት
ዛፉ አርቃኑን ፈትሎ ለብሶ 
ሳሩ በነጭ ጭቃ ተለውሶ
አፌ የዉርጭ ነበልባል አየተፋ
እግሬ ሰማይ ያቦካውን ሊጥ አየገፋ...
በርዳ'ማትበርደው ነፍሴ
ላፍታ አፈትልካ ከዉርጩ ናዳ
በዱቄት ዳመና ሰርጋ ነጉዳ
ያገሬን ለጋስ ጠሃይ ሞቃ ሞቃ
ሳታገግም ፣ ሳትጠረቃ
በቆፈን ላብ ተጠምቄ ፣ ከቁም ድንዛዜ ስነቃ...
አገኘሁት በድን ገላዬን ፣ ከጭጋጋማው ከተማ
ዋቲው ማቲው ተከናንቦ ፣ አጫ በረዶ ሸማ።

ገንዘብና ዝና

ጥሙን ላፍታ ገትቶ ለመረመራቸው
ገንዘብና ዝና ፣ የባህር ዉሃ ናቸው
በተጠጡ ቁጥር ፣ የሚብስ ጥማቸው።