ማክሰኞ 17 ዲሴምበር 2013

እኔ ማነኝ?

የሰው ስህተት ለማመልከት፣
ከብርሃን ፈጥኜ የምከሰት

ጥያቄማ ተጠይቄ?
አላውቅምን የት አዉቄ

ግልፅነቴና ድፍረቴ፣
ወይ በብቅል ወይ በእብደቴ

ሲነሳ ጉድለት ድክመቴ፣
ላብ በላብ አጥንት ጅማቴ

እያረረ የቤቴ ድስት፣
የማማስል የጎረቤት

እኮ ታዲያ እኔ ማነኝ?

በመምሰል ያላወቃችሁኝ፣
ካንገት በላይ አታስቁኝ፣
እንቆቅልሼን መልሱልኝ፣
ካሰኛችሁም ሀገር ስጡኝ፣
እኔ ግን የናንተው ልጅ ነኝ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ