ባዶ አንጀቱ እንደቆሰለ
ፊቱ በንዳድ እንደከሰለ
ቆራጥ ሃሞቱን እንደቋጠረ
ልጄ እንደወጣ በቀረ...
ያዘን ጎርፍ ገፍቶኝ ፣ ቢጥለኝ ፊታቸው
ተሽቀርቅረው መጡ ፣ በዋና ልብሳቸው
የ'ንባዬ ቦይ ስፋት ፣ ዉቅያኖስ መስሏቸው።
ልጄስ ወድቆ ቀረ ፣ ላንዴ እስከ ወዲያኛው
ምሬቴን ማርከሻ ፣ ምን ይሆን መፅናኛው?
ለፍርድ መማፀኛ ፣ በተዘረጋ እጄ
እዝን አስጨበጡኝ ፣ ጅብ ለበላው ልጄ።
-----------------------------------------
(ከተኩላ ሲሸሹ በጅብ ለተበሉት)
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ