ቅኔ ናት ሀገሬ ፣ ባለ ሰምና ወርቅ አስለቃሿን ስታይ ፣ ከ'ት ብላ ምትስቅ።ሀገሬ ቅኔ ናት ፣ ባለ ሰምና ወርቅ
ሚያከስላትን እቶን ፣ ለቆፈኗ ምትሞቅ።
ቅኔ ናት ሀገሬ ፣ ባለ ወርቅና ሰም
ባላንጣዋን አቅፋ ፣ አጥብቃ ምትስም።
ባዶ አንጀቱ እንደቆሰለ ፊቱ በንዳድ እንደከሰለ ቆራጥ ሃሞቱን እንደቋጠረ
ልጄ እንደወጣ በቀረ...
ያዘን ጎርፍ ገፍቶኝ ፣ ቢጥለኝ ፊታቸው
ተሽቀርቅረው መጡ ፣ በዋና ልብሳቸው
የ'ንባዬ ቦይ ስፋት ፣ ዉቅያኖስ መስሏቸው።
ልጄስ ወድቆ ቀረ ፣ ላንዴ እስከ ወዲያኛው
ምሬቴን ማርከሻ ፣ ምን ይሆን መፅናኛው?
ለፍርድ መማፀኛ ፣ በተዘረጋ እጄ
እዝን አስጨበጡኝ ፣ ጅብ ለበላው ልጄ።
-----------------------------------------
(ከተኩላ ሲሸሹ በጅብ ለተበሉት)