ሰኞ 14 ዲሴምበር 2015

ፍቱን

ቃል ሲመነምን ሲቀጭጭ
አንደበት ሲነጥፍ ሲል ረጭ
አይገለጤን መግለጫ
ዝምታ ፍቱን ማምለጫ።

የለዉም ዋጋ

ሰላም የናኘ ቢመስልም 
ፈገግታ ሞልቶ ቢፈስም 
ጥርሶች ለሳቅ ቢሽቀዳደሙ 
ነጫጭ እርግቦች ከትከሻው ቢከትሙ
ይህ ሁሉ የለዉም ዋጋ 
ሰው ከራሱ ከተዋጋ።