በጦርታችን ሰላም፣
በባርነታችን ነፃነት
በድቀታችን ጥንካሬ፣
በድንቁርናችን እውቀት
ኑ እንያያዝ እጅ ለእጅ
ኑ ተባብረን እንደርጅ ።
ሽንቁር እንስራ ደቅነን፣
ኑ ከሙሉ ባህር እንጥለቅ
የዋና ብስና እያገሳን፣
ኑ ከድቅድቅ ዝቅጠት እንዝለቅ።
ሆኖልን አያውቅምና፣
የፍቅርን አዝመራ ማጨድ
በነፋስ ሳቅ እንዲፈርሱ፣
ሞኝ ዱቄትና አመድ።
እሑድ 8 ኖቬምበር 2015
ማን? መቼ?
ልብሽ ከልቤ እንዲዋሃድ
ደጅ ብጠና ስለመውደድ
ቀና ብለሽ ካንገትሽ
"እሱ ያለ 'ለት" ካልሽኝ
አመታት እንደዋዛ አለፉኝ።
ቆመው ሊቀሩ የነበሩ
አረፍ ሲሉ ከወንበሩ
አለሁ እንዳየሁ ወደ ላይ
"እሱ" ያልሽው ሳይገባኝ፣
እግዜርን ይሆን ወይ ሰማይ
አለሁ ሲመሽ ሲነጋ
ያንን እለት ፍለጋ።
ደጅ ብጠና ስለመውደድ
ቀና ብለሽ ካንገትሽ
"እሱ ያለ 'ለት" ካልሽኝ
አመታት እንደዋዛ አለፉኝ።
ቆመው ሊቀሩ የነበሩ
አረፍ ሲሉ ከወንበሩ
አለሁ እንዳየሁ ወደ ላይ
"እሱ" ያልሽው ሳይገባኝ፣
እግዜርን ይሆን ወይ ሰማይ
አለሁ ሲመሽ ሲነጋ
ያንን እለት ፍለጋ።
ማክሰኞ 3 ኖቬምበር 2015
ልንገርሽ'ማ
ያንቺ ብርቱ በሽታሽ
ያንቺ ክፉ ነቀርሳሽ ...
እንዳይመስልሽ ሆደ-ቅሪላ ጉበኛ
አይምሰልሽ ፍርድ ሚገመድል ዳኛ
እንዳይመስልሽ በሰፊ ምድርሽ ጠቦ አጥባቢ
አይምሰልሽ ታሪክ ደልዞ ቅራቅንቦ ከታቢ ...
ያንቺ ብርቱ በሽታሽ
ያንቺ ክፉ ነቀርሳሽ ...
እንዳይመስልሽ ድንበርሽን ጥሶ የመጣ
ከቶ አይምሰልሽ ያ ፀጉረ ለዋጣ ...
ያንቺ'ማ የጎን ዉጋትሽ!
ያንቺ'ማ የግር እሳትሽ!
ያንቺ'ማ ክፉ ደመኛሽ!
ያንቺ'ማ እኩይ ቀበኛሽ! ...
በአፍራሾችሽ ትብብር ፣ጠልቆ ሲቆፈር ጉድጓድሽ
አካፋ ዶማ ያቀበልኩ ፣ እኔው ራሴ ነኝ ጠላትሽ!
ያንቺ ክፉ ነቀርሳሽ ...
እንዳይመስልሽ ሆደ-ቅሪላ ጉበኛ
አይምሰልሽ ፍርድ ሚገመድል ዳኛ
እንዳይመስልሽ በሰፊ ምድርሽ ጠቦ አጥባቢ
አይምሰልሽ ታሪክ ደልዞ ቅራቅንቦ ከታቢ ...
ያንቺ ብርቱ በሽታሽ
ያንቺ ክፉ ነቀርሳሽ ...
እንዳይመስልሽ ድንበርሽን ጥሶ የመጣ
ከቶ አይምሰልሽ ያ ፀጉረ ለዋጣ ...
ያንቺ'ማ የጎን ዉጋትሽ!
ያንቺ'ማ የግር እሳትሽ!
ያንቺ'ማ ክፉ ደመኛሽ!
ያንቺ'ማ እኩይ ቀበኛሽ! ...
በአፍራሾችሽ ትብብር ፣ጠልቆ ሲቆፈር ጉድጓድሽ
አካፋ ዶማ ያቀበልኩ ፣ እኔው ራሴ ነኝ ጠላትሽ!
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)