ያንቺ ብርቱ በሽታሽ
ያንቺ ክፉ ነቀርሳሽ ...
እንዳይመስልሽ ሆደ-ቅሪላ ጉበኛ
አይምሰልሽ ፍርድ ሚገመድል ዳኛ
እንዳይመስልሽ በሰፊ ምድርሽ ጠቦ አጥባቢ
አይምሰልሽ ታሪክ ደልዞ ቅራቅንቦ ከታቢ ...
ያንቺ ብርቱ በሽታሽ
ያንቺ ክፉ ነቀርሳሽ ...
እንዳይመስልሽ ድንበርሽን ጥሶ የመጣ
ከቶ አይምሰልሽ ያ ፀጉረ ለዋጣ ...
ያንቺ'ማ የጎን ዉጋትሽ!
ያንቺ'ማ የግር እሳትሽ!
ያንቺ'ማ ክፉ ደመኛሽ!
ያንቺ'ማ እኩይ ቀበኛሽ! ...
በአፍራሾችሽ ትብብር ፣ጠልቆ ሲቆፈር ጉድጓድሽ
አካፋ ዶማ ያቀበልኩ ፣ እኔው ራሴ ነኝ ጠላትሽ!
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ