የብርሃኑ ስንኞች
የስነ-ግጥም ጦማር
Home
About
ረቡዕ 30 ኦገስት 2017
ባንድ አምባ
ነጋ፣
ቀን ሌትን ፈንግሎ፣ ባምባው ሊገንበት
ሰው ሕልሙን ሊራመድ፣ ነቃ ከተኛበት
ሲማስን - ሲኳትን፣ አይተጉ ሲተጋ
ላልጨበጠው አልፋ፣ ኦሜጋ ፍለጋ
መሸ፣
ፍጥረት አፏሸከ፣ አይዘጉት አዛጋ
ሁሉም ተከተተ፣ ሁሉም በሩን ዘጋ
ሲያፈጥ እንዳልዋለ፣ ቀን አይኑን ከደነ
በእንቅልፍ ቡልኮ፣ መስሚያዉን ሸፈነ
ሌት ሆይ ባለተራው፣ አምባገነን ሆነ።
ረቡዕ 16 ኦገስት 2017
ክቡራን ሸኝዎች
ሕይወት ሸኝታችሁ፣ ሃውልት ልታኖሩ
በእድሩ ጥሩንባ፣ ቀበቶ እምታስሩ
ለሂያጅ መታወሻ
ለሞቱ ማርከሻ
ብረት ስታቀልጡ
አለት ስትፈልጡ
አፈር ስታቦኑ
አሸዋ ስትዘግኑ
ነፍሱን እንዲደላት፣ በአፀደ-ገነት
ስትገቡ ሱባኤ፣ በደብር ሰገነት
ይልቅ አንድ ነገር፣ ጠይቁ መርምሩ
የት ጋር እንደሆነ፣
ቀሪዉን ከሂያጁ፣ መለያ መስመሩ።
በጣም አዲስ ልጥፎች
በጣም የቆየ ልጥፍ
መነሻ
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)