ረቡዕ 16 ኦገስት 2017

ክቡራን ሸኝዎች

ሕይወት ሸኝታችሁ፣ ሃውልት ልታኖሩ
በእድሩ ጥሩንባ፣ ቀበቶ እምታስሩ
ለሂያጅ መታወሻ
ለሞቱ ማርከሻ
ብረት ስታቀልጡ
አለት ስትፈልጡ
አፈር ስታቦኑ
አሸዋ ስትዘግኑ
ነፍሱን እንዲደላት፣ በአፀደ-ገነት
ስትገቡ ሱባኤ፣ በደብር ሰገነት
ይልቅ አንድ ነገር፣ ጠይቁ መርምሩ
የት ጋር እንደሆነ፣
ቀሪዉን ከሂያጁ፣ መለያ መስመሩ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ