እደጅ እንዳላድር
ኮከብ እንዳልቆጥር
ከሩቅ አብረቅራቂ፣
አብሪ - ተወርዋሪ፣ ኮከቦች አለቁ
ከሰማይ ላይ ወልቀው፣ ካፈር ተጠለቁ
ምድር ባደይ ኮከብ፣ ተኩላ ቢያዩ
ታምራት አውጀው፣ ዓሶች በረገጉ
ዉቅያኖስ እንግተው፣ ከንፌ-አውጪኝ አረጉ
ዉሃውና ዓሳው፣ ሰማይ ከከተሙ
ክዋክብት አምረው፣ ቁልቁል ከተመሙ
ከዘመን ጋር ዘምኗል፣ ኩርማንን ፍለጋ
ሽቅብ አያንጋጠጥን፣ መረብ እንዘርጋ።
እሑድ 10 ሴፕቴምበር 2017
ቅዳሜ 2 ሴፕቴምበር 2017
እሳትና ዉሃ
እብሪት እንደዝናር፣ አጥብቀው በሚያስሩ
ክብሪት እንደክራር፣ በሚደረድሩ
በእፍባዮች ምድር፣ በቆስቋሾች ዓለም
መሆንህን ረስተህ፣ አንድ ዘለላ ፍም
የኔን ጠብታነት፣ ቁልቁል እያየሃት
መሆንህን ነገርከኝ፣ የማትከስም እሳት
እድሜ ለዝናቡ፣
አጭዶ ለሚወቃው፣ የዶፉን አዝመራ
ተግቶ ለሚሞላው፣ የውቅያኖስ ጎተራ
ምስጋና ለንፋስ፣
ሳይታክት ለሚሰጥ፣
ለጡዘትህ ቤንዚን
ለእብደትህ እስትንፋስ
ባንድነት ለመጥፋት፣ እንዳልተፋለግን
እልፎች እንዲፀድቁ፣ አብረን ጠወለግን።
ክብሪት እንደክራር፣ በሚደረድሩ
በእፍባዮች ምድር፣ በቆስቋሾች ዓለም
መሆንህን ረስተህ፣ አንድ ዘለላ ፍም
የኔን ጠብታነት፣ ቁልቁል እያየሃት
መሆንህን ነገርከኝ፣ የማትከስም እሳት
እድሜ ለዝናቡ፣
አጭዶ ለሚወቃው፣ የዶፉን አዝመራ
ተግቶ ለሚሞላው፣ የውቅያኖስ ጎተራ
ምስጋና ለንፋስ፣
ሳይታክት ለሚሰጥ፣
ለጡዘትህ ቤንዚን
ለእብደትህ እስትንፋስ
ባንድነት ለመጥፋት፣ እንዳልተፋለግን
እልፎች እንዲፀድቁ፣ አብረን ጠወለግን።
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)