እሑድ 4 ኖቬምበር 2018

እልልፎሽ

ወንዝ ባልዞረበት ድልድይ ስንዘረጋ
ምሰሶው ሳይጠና ደጃፍ ስንዘጋ
ለመላጣ እራስ ሚዶ ስንመትር
ለመከነ አዝመራ ነዶ ስንከምር
በለበጣ ስሌት አብሮነት ሲለካ
ምኞቴን ለፍፈህ፣ ምኞትክን አሳካ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ