"ማወቅ ሙሉ ያደርጋል" አሉን አዋቂዎች
ከቅርብ እያደሩ ፣ ተሩቅ ለምላሚዎች
የዋህነታቸው ፣ አለ-ማወቃቸው
ባዶዉን ጎደሎ ፣ አርገው ማየታቸው።
ሆኖ ታያውቅ ፣ ማወቅ ምሉእነት
ምጥቀት ፣ ባስተሳሰብ ገናናነት
ካ'ቻ'ንጎል መመንጠቅ ፣ ባተያይ ፣ በጢነት።
የማወቅስ ወጉ
ግፋ ቢልም ጥጉ
ወንፊትና ቁና ፣ ካ'ቻላይ ሳይነጥቁ
አንጓሎ ማጣራት ፣ ማወቅን ታ'ለማወቁ።
ባውቃለሁ ሳይረ'ቁ ፣ ሳይመፃደቁ
ማወቅን ከምግባር ፣ ሳይዋሹ ማስታረቁ።
ረቡዕ 31 ዲሴምበር 2014
ሰኞ 15 ዲሴምበር 2014
ረቡዕ 10 ዲሴምበር 2014
ማክሰኞ 9 ዲሴምበር 2014
መርቀኝ ላልከኝ ወዳጄ
ሸለቆው ሜዳ እንዲሆንልህ
የማይሰበር እምነት ይስጥህ
የአይቻልም ተራራውን ከቶ አትፍራው
በፅኑ እምነትህና ትግስትህ ቦርቡረው
ቢጠፋ ቢጠፋ
አንድ የተስፋ ጠጠር መፈልቀቅ አይከፋ።
በቀቢፀ-ተስፋ ሸለቆ ተዉጠህ ሳለህም
በአለት ጣሪያና ግድግዳ ተከበህ ሳለህም
ዉድ ወዳጄ አይንሳህ የእዉን ሕልም።
ጨረስኩ አሜን አትልም?
ለምርቃት እኮ ምርቃት የለዉም :-)
የማይሰበር እምነት ይስጥህ
የአይቻልም ተራራውን ከቶ አትፍራው
በፅኑ እምነትህና ትግስትህ ቦርቡረው
ቢጠፋ ቢጠፋ
አንድ የተስፋ ጠጠር መፈልቀቅ አይከፋ።
በቀቢፀ-ተስፋ ሸለቆ ተዉጠህ ሳለህም
በአለት ጣሪያና ግድግዳ ተከበህ ሳለህም
ዉድ ወዳጄ አይንሳህ የእዉን ሕልም።
ጨረስኩ አሜን አትልም?
ለምርቃት እኮ ምርቃት የለዉም :-)
ሰኞ 1 ዲሴምበር 2014
ላልራመድ - ላልበር
ልቤ ገስግስ ይለኛል
ናፍቀሃል አግኛት ይለኛል
ገስግሼ መጣበት ፣ ጉልበትማ ነበረኝ
ካለሽበት ደርስበት ፣ ፅናትማ ነበረኝ
ብቻ አንድ ነገር ፣ አይቸግሩ ቸገረኝ...
ላብሮነታችን መሳካት ፣ የተስፋ ስንቄን ቋጥሬ
በቃልኪዳናችን መቀነት ፣ ቀጭን ወገቤን አስሬ
እግሬን ባቅጣጫሽ ቃኝቼ ፣ ለመራመድ ሲዳዳኝ
ሰርክ ወዳዘዝኩት ስፍራ ፣ ሳያቅማማ 'ሚወስደኝ
ልቤ መምጣትን ቢሻም ፣ እግሬ ላይሄድ ሞገተኝ...
የሚወደን ፣ የምንወደው
ያ ደጋጉ ፣ ያገር ሰው
"ጉድ ሳይሰማ..." ፣ አይደል 'ሚለው?
እውነት እኮ ፣ እዉነት አለው
ጆሮ አይሰማው የለ ፣ ስሚው...
ትዝ ይልሻል ያ መስካችን?
የነፃነት አየር መማጊያችን
በሰማያዊ ጣሪያ ተከልሎ ፣ ባረንጓዴ ምንጣፍ የተዋበው
ቀኑን በፀሐይ ዉጋጋን ፣ ሌቱን በጨረቃ ብርሃን 'ሚደምቀው
የት ጀምሮ የት ይለቅ ፣ ለ'ኛ ጉዳይ ያልነበረው
የባለ-ርስቱ ማንነት ፣ ድንበሩ ደንታ 'ማይሰጠን
ትንፋሻችን እስኪሟጠጥ ፣ ሳይታክት 'ሚያስቦርቀን...
ትዝ ይልሻል ሰበብ-አልባ ፍቅራችን?
ያልጠለሸው ልቦናችን ፣ ያልተበረዘው መንፈሳችን
በከዋክብት ጭብጨባ ታጅበን ፣ ነፍሴ ከነፍስሽ ስትዋሃድ
በፍቅር መንኩራኩር ተሳፍረን ፣ ከጠፈር ጠፈር ስንነጉድ
ብንካፈል - ብናካፍል ፣ ፍቅርና ፍቅርን ብቻ
ብንዘራ - ብንሰበስብ ፣ ፍቅርና ፍቅርን ብቻ
አይን ፣ ጆሮ ፣ ልብ የሌለን ፣ ለክፋትና ለጥላቻ...
አሁን ትዝ አለሽ ያ መስካችን?
የነፃነት አየር መማጊያችን...
እናልሽ፣ ቅድም ስነግርሽ
እግሬ ሞገተኝ ነበር ያልኩሽ?
ያለ ምክንያት እንዳይመስልሽ
ዝርዝሩ ከቶም አይረባሽ
ፍሬ-ነገሩን ብቻ ላውጋሽ...
ለመንገዱ ቁብ ሳልሰጥ፣ የመድረስ ጉጉት ስያቋምጠኝ
እግሬ እውነት ነበረው ፣ ላይራመድ ቢያብልብኝ
ያቅጣጫዬ ቅኝቱ ፣ ለእግሬ ምቱ ጠፍቶበታል
የነበረው በሙሉ ፣ እንዳልነበር ሆኖበታል
ያ ዉቡ መስካችን ፣ በ'ርቃን አለት ተተክቷል
ያ ደጋጉ ያገር ሰው ፣ ልቦናው ክፉኛ ደንድኗል
መስኩ ባየው ሆድ ብሶት ፣ እግሬ አውጣኝ ሸምጧል
ጨርቅ ማቁን ሳይሸክፍ ፣ አገር ጥሎ ኩብልሏል
መላወሻ የሌለው ፣ ዙሪያ ገባው ገደል ሆኗል።
ጉልበቴን ከፅናቴ ፣ በተስፋ ዉል አጣምሬ
መራመድ የተሳነኝ ፣ መቆሚያ አጥቶ እግሬ
ለምን አንደሆነ ፣ አሁን ገባሽ ፍቅሬ?
አንቺ'ኮ ንፁህ ተስፈኛ ነሽ
ደግ ደጉ ብቻ 'ሚታይሽ
መራመድ ከተሳነህ ፣ በርረህ ና የምትይው
ዉዴ ሌላ ፈተና አለ ፣ በጭራሽ ያላየሽው
ካማልእክት ብዋስም ፣ ክንፍ ለመብረርያ
እንዴት ልመንጠቀው ፣ ያለ መንደርደርያ?!
ናፍቀሃል አግኛት ይለኛል
ገስግሼ መጣበት ፣ ጉልበትማ ነበረኝ
ካለሽበት ደርስበት ፣ ፅናትማ ነበረኝ
ብቻ አንድ ነገር ፣ አይቸግሩ ቸገረኝ...
ላብሮነታችን መሳካት ፣ የተስፋ ስንቄን ቋጥሬ
በቃልኪዳናችን መቀነት ፣ ቀጭን ወገቤን አስሬ
እግሬን ባቅጣጫሽ ቃኝቼ ፣ ለመራመድ ሲዳዳኝ
ሰርክ ወዳዘዝኩት ስፍራ ፣ ሳያቅማማ 'ሚወስደኝ
ልቤ መምጣትን ቢሻም ፣ እግሬ ላይሄድ ሞገተኝ...
የሚወደን ፣ የምንወደው
ያ ደጋጉ ፣ ያገር ሰው
"ጉድ ሳይሰማ..." ፣ አይደል 'ሚለው?
እውነት እኮ ፣ እዉነት አለው
ጆሮ አይሰማው የለ ፣ ስሚው...
ትዝ ይልሻል ያ መስካችን?
የነፃነት አየር መማጊያችን
በሰማያዊ ጣሪያ ተከልሎ ፣ ባረንጓዴ ምንጣፍ የተዋበው
ቀኑን በፀሐይ ዉጋጋን ፣ ሌቱን በጨረቃ ብርሃን 'ሚደምቀው
የት ጀምሮ የት ይለቅ ፣ ለ'ኛ ጉዳይ ያልነበረው
የባለ-ርስቱ ማንነት ፣ ድንበሩ ደንታ 'ማይሰጠን
ትንፋሻችን እስኪሟጠጥ ፣ ሳይታክት 'ሚያስቦርቀን...
ትዝ ይልሻል ሰበብ-አልባ ፍቅራችን?
ያልጠለሸው ልቦናችን ፣ ያልተበረዘው መንፈሳችን
በከዋክብት ጭብጨባ ታጅበን ፣ ነፍሴ ከነፍስሽ ስትዋሃድ
በፍቅር መንኩራኩር ተሳፍረን ፣ ከጠፈር ጠፈር ስንነጉድ
ብንካፈል - ብናካፍል ፣ ፍቅርና ፍቅርን ብቻ
ብንዘራ - ብንሰበስብ ፣ ፍቅርና ፍቅርን ብቻ
አይን ፣ ጆሮ ፣ ልብ የሌለን ፣ ለክፋትና ለጥላቻ...
አሁን ትዝ አለሽ ያ መስካችን?
የነፃነት አየር መማጊያችን...
እናልሽ፣ ቅድም ስነግርሽ
እግሬ ሞገተኝ ነበር ያልኩሽ?
ያለ ምክንያት እንዳይመስልሽ
ዝርዝሩ ከቶም አይረባሽ
ፍሬ-ነገሩን ብቻ ላውጋሽ...
ለመንገዱ ቁብ ሳልሰጥ፣ የመድረስ ጉጉት ስያቋምጠኝ
እግሬ እውነት ነበረው ፣ ላይራመድ ቢያብልብኝ
ያቅጣጫዬ ቅኝቱ ፣ ለእግሬ ምቱ ጠፍቶበታል
የነበረው በሙሉ ፣ እንዳልነበር ሆኖበታል
ያ ዉቡ መስካችን ፣ በ'ርቃን አለት ተተክቷል
ያ ደጋጉ ያገር ሰው ፣ ልቦናው ክፉኛ ደንድኗል
መስኩ ባየው ሆድ ብሶት ፣ እግሬ አውጣኝ ሸምጧል
ጨርቅ ማቁን ሳይሸክፍ ፣ አገር ጥሎ ኩብልሏል
መላወሻ የሌለው ፣ ዙሪያ ገባው ገደል ሆኗል።
ጉልበቴን ከፅናቴ ፣ በተስፋ ዉል አጣምሬ
መራመድ የተሳነኝ ፣ መቆሚያ አጥቶ እግሬ
ለምን አንደሆነ ፣ አሁን ገባሽ ፍቅሬ?
አንቺ'ኮ ንፁህ ተስፈኛ ነሽ
ደግ ደጉ ብቻ 'ሚታይሽ
መራመድ ከተሳነህ ፣ በርረህ ና የምትይው
ዉዴ ሌላ ፈተና አለ ፣ በጭራሽ ያላየሽው
ካማልእክት ብዋስም ፣ ክንፍ ለመብረርያ
እንዴት ልመንጠቀው ፣ ያለ መንደርደርያ?!
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)