ረቡዕ 31 ዲሴምበር 2014

ማወቅ

"ማወቅ ሙሉ ያደርጋል" አሉን አዋቂዎች
ከቅርብ እያደሩ ፣ ተሩቅ ለምላሚዎች
የዋህነታቸው ፣ አለ-ማወቃቸው
ባዶዉን ጎደሎ ፣ አርገው ማየታቸው።
ሆኖ ታያውቅ ፣ ማወቅ ምሉእነት
ምጥቀት ፣ ባስተሳሰብ ገናናነት
ካ'ቻ'ንጎል መመንጠቅ ፣ ባተያይ ፣ በጢነት።
የማወቅስ ወጉ
ግፋ ቢልም ጥጉ
ወንፊትና ቁና ፣ ካ'ቻላይ ሳይነጥቁ
አንጓሎ ማጣራት ፣ ማወቅን ታ'ለማወቁ።
ባውቃለሁ ሳይረ'ቁ ፣ ሳይመፃደቁ
ማወቅን ከምግባር ፣ ሳይዋሹ ማስታረቁ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ