እንዳንድ ቀን አለ፣
ምናብን እንዳክናፍ ፣ በሰፊ አዘርግቶ
ብረር ብረር ሚል ፣ ከምድር አስነስቶ።
ደሞ አለ አንዳንድ ቀን፣
ቢሆንን ሚያስመኝ ዘላለም አንድ ቀን
ጠራርጎ የሚሸኝ የ'ላዌን ሰቀቀን።
አንዳንድ ቀን አለ፣
ሳይጠሩት አቤት ባይ
ሳይልኩት ወዴት ባይ
ይሉትን አይሰማ ፣ ቃላባይ እንዳ'ባይ።
ደሞ አለ አንዳንድ ቀን፣
የቀን ባለቅኔ
በቆፈን ቆርብተህ ፣ ተቆራምተህ ሲያይህ
ሳጥን ሙሉ እርዛት፣ ደራርቦ ሚያለብስህ
ሌማት ሙሉ ጠኔ፣ ፈትፍቶ ሚያጎርስህ
እንጀትክን ሊያርስህ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ