ዓርብ 1 ዲሴምበር 2017

ተጠየቅ እረኛ

ጠረቃሁ ለማታውቅ፣ ብትጠጣ ብትበላ
ለዚህች ለራስ ወዳድ፣ ላንዲት ከርስ ተድላ
ከገል ለተበጀች፣ ቁንፅል የዕድሜ ጀምበር
ዋስትና ለሌላት፣ ከሴኮንድ በኋላ እንደማትሰበር
ስንደዶ ቀንጥሰን፣ የገመድነው ጅራፍ
መልሶ ገረፈን፣ ባጦዝነው ሺህ እጥፍ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ