ድንቅነትሽ እጡብ ድንቅ
ጨቅላ ፍጡር የሚያስቦርቅ
ነፀብራቅሽ ዘንጉ ረዥም
ከሰሜን ዋልታ አንስቶ፣
እስካንታርክቲካ የሚያንፀባርቅ
ያይኖችሽ ጦር ሰበቃ
ከሞት ታናሽ ወንድም፣
ብርሌ ነፍስ የሚያነቃ
ፈገግታሽ ላድማስ ቦግታው
የደመናትን መንጋ፣ ከሰማይ ላይ የሚመታው
ካለው፣ ካልነበረው
ከሌለው፣ ከሚኖረው
ተጣጥተን፣ ተፋልገን
ተራርበን፣ ተጣግበን
ዉል አልባ ተጣልፈን
አይፈቱት ተቋልፈን
ነግቶ እማኝ እንዳይሆን፣ አንሶላ ቀደድን
ክዋክብት ተጋፈን፣ በሸንጎ ቀለድን።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ