ፅልመትን ሸኝተን ፣ ብርሃን ልናበስር
ተኮልኩለን ነበር ፣ ከትልቅ ዋርካ ስር
ከፍታን ለማየት ፣ ሲቃና አንገታችን
በዋርካው ቅጠሎች ፣ ተጋረደ አይናችን
ከዋርካው በስተላይ፣ ከጥላው ባሻገር
አድማስ ይንጣ ይጥቆር ፣ አልገባንም ነበር።
ባ'ንድ በገዳም ቀን
ባ'ንድ ክንድ አብረን
ያንን ግዙፍ ጥላ ፣ ያንን ግዙፍ ዋርካ
ገዝግዘን…
ገዝግዘን…
ከስር መሰረቱ ፣ ነቅለን ስናበቃ
ፀሐይ አሸልባ ፣ ነቅታለች ጨረቃ።
ሰኞ 29 ሴፕቴምበር 2014
ሐሙስ 25 ሴፕቴምበር 2014
ማንም - ከየትም
'ማልመደብ ከክርስቲያኑ ፣ ከሙስሊሙ ወይ ካ'ይሁዱ
'ማልፈረጅ ከቡድሃው ፣ ከሱፊው ፣ ከዜኑ ወይ ከሂንዱ
ከሃይማኖት ወይ ከባህል 'ማይመራኝ መንገዱ
ያልመጣሁ ከምሥራቁ ወይ ከምዕራቡ
ያ'ይደለሁ ከሰሜኑ ወይ ከደቡቡ
ያልፈለቅሁ ከባህሩ ፣ ከጥልቁ ከውቅያኖሱ
ያልወረድሁ ከደመናው ፣ ከሰማያዊ ክርታሱ
ከትቦ ያላስቀመጠኝ ፣ የፍጥረት ሀተታ ድርሳን
ዘሬ ግንዱ 'ማይመዘዝ ፣ ካ'ዳም እና ከሔዋን
ስፍራዬ ስፍራ የሌለዉ ሊጎበኘኝ ለሚተጋ
ዱካዬ ዱካው 'ማይገኝ የሚፈትን ለፍለጋ
መደብ ያልተበጀልኝ ከመንፈስ ወይ ከሥጋ
አይደለሁኝ ማንም
አይደለሁም የማንም
ከዚህኛዉ የለሁም
አልኖር ከሚመጣዉም
ያልመጣሁኝ ከየትም
የማልሄድ ወደ የትም
ማንም ነኝ ከየትም።
***********************
የ "Rumi"ን "Only Breath" የተሰኘዉን ግጥም አንብቤ ሳበቃ በ'ኔው ገልቱ ትርጉም ወደ አማርኛ የተቀየረ
'ማልፈረጅ ከቡድሃው ፣ ከሱፊው ፣ ከዜኑ ወይ ከሂንዱ
ከሃይማኖት ወይ ከባህል 'ማይመራኝ መንገዱ
ያልመጣሁ ከምሥራቁ ወይ ከምዕራቡ
ያ'ይደለሁ ከሰሜኑ ወይ ከደቡቡ
ያልፈለቅሁ ከባህሩ ፣ ከጥልቁ ከውቅያኖሱ
ያልወረድሁ ከደመናው ፣ ከሰማያዊ ክርታሱ
ከትቦ ያላስቀመጠኝ ፣ የፍጥረት ሀተታ ድርሳን
ዘሬ ግንዱ 'ማይመዘዝ ፣ ካ'ዳም እና ከሔዋን
ስፍራዬ ስፍራ የሌለዉ ሊጎበኘኝ ለሚተጋ
ዱካዬ ዱካው 'ማይገኝ የሚፈትን ለፍለጋ
መደብ ያልተበጀልኝ ከመንፈስ ወይ ከሥጋ
አይደለሁኝ ማንም
አይደለሁም የማንም
ከዚህኛዉ የለሁም
አልኖር ከሚመጣዉም
ያልመጣሁኝ ከየትም
የማልሄድ ወደ የትም
ማንም ነኝ ከየትም።
***********************
የ "Rumi"ን "Only Breath" የተሰኘዉን ግጥም አንብቤ ሳበቃ በ'ኔው ገልቱ ትርጉም ወደ አማርኛ የተቀየረ
ሐሙስ 18 ሴፕቴምበር 2014
ስካር
በላይ በላዩ ላይ ስትጨልጥ አምሽተህ
ከሚጠጣ ነገር ሽጉጥ ብቻ ቀርቶህ
ጎህ ሲቀድ ሰማይ በቀዝቃዛ ጠዋት
"የት ገባ ራስ ምታት?"
"የት ገባ ማዛጋት?"
እያልክ አትሸበር
በፍቅር ሲሰከር
የለዉም ሀንጎቨር።
ከሚጠጣ ነገር ሽጉጥ ብቻ ቀርቶህ
ጎህ ሲቀድ ሰማይ በቀዝቃዛ ጠዋት
"የት ገባ ራስ ምታት?"
"የት ገባ ማዛጋት?"
እያልክ አትሸበር
በፍቅር ሲሰከር
የለዉም ሀንጎቨር።
ረቡዕ 17 ሴፕቴምበር 2014
ሰኞ 15 ሴፕቴምበር 2014
ስለ ሞገደኛው ፍቅርሽ
ላወጋሽ ስከጅል ፣ ታሪኬን ዘርዝሬ
በትዝታ ክንፌ ፣ የኋሊት በርሬ
ድው! ድው! እያለ ፣ እንደ ጠንቋይ ዲቤ
በጉግስ ትርታ ፣ እየመታ ልቤ
ከወዳደቀበት ፣ ትንፋሼን ሰብስቤ
የድፍረትን አየር ፣ በረ....ዥሙ ስቤ
በብርክ ማዕበል ዉስጥ እንደተሳከረ
ከወዲያ ከማዶ ይጣራ የነበረ
አስገምጋሚው ድምፄ ፣ ጭጭ ብሎ ቀረ።
ሻል ያለኝ ሲመስለኝ
እንዲህም አስመኘኝ
ቃላት ከፊደላት ሰብስቤ
ሃሳብ ባ'ሳብ ላይ ደርቤ
አንደበቴ ተሞርዶ እንዳለቀ
ሃሳቤ ባ'ንዳፍታ ተፍረከረከ
ድንጋይ አንደመታው መስታወት ተሰነጠቀ።
በማዕበላማው የፍቅር ባህርሽ
ጀልባዬ ብትሰጥም አይግረምሽ
እንኳንስ የ'ኔ ኢምንት ጀልባ
ካንቺ ዉብ አይን ከቶ 'ማትገባ
ተወርዋሪው የፍቅርሽ ማዕበል
ግዙፉን መርከብም ያሰጥማል።
የፍቅርሽ ወጀብ ብርታቱ
ተተርኮ ላይዘለቅ ጥልቀቱ
ኮስማና ጀልባዬን አንስቶ
ካ'ለት ከቋጥኙ አጋጭቶ
ያረጀ አካላቷን ፈታትቶ
መደገፊያ ዘንጌን ነስቶ
አንደ'ዜ በፍቅርሽ ማዕበል ስደገፍ
ሌላ'ዜ በወጀቡ ተገፍቼ ስንሳፈፍ
ለይቼ ሳላውቅ ኩነቴን
መኖሬን ወይ አለመኖሬን
መሆኔን ቆሜ ሳበስር
አለመሆኔ ሲነቅለኝ ከሥር
በመኖሬ መኖር ሳጓራ
አለመኖሬ ገዝፎ ከጋራ
ወዲህ ረከስኩ ብዬ ስቆዝም
ወዲያ ዋጋዬ ንሮ ስደመም
ስሞት ስነሳ በፍቅር
ስለ ትንሣኤ መኖር
ከቶ እንዴት ብዬ ልጠራጠር?
በትዝታ ክንፌ ፣ የኋሊት በርሬ
ድው! ድው! እያለ ፣ እንደ ጠንቋይ ዲቤ
በጉግስ ትርታ ፣ እየመታ ልቤ
ከወዳደቀበት ፣ ትንፋሼን ሰብስቤ
የድፍረትን አየር ፣ በረ....ዥሙ ስቤ
በብርክ ማዕበል ዉስጥ እንደተሳከረ
ከወዲያ ከማዶ ይጣራ የነበረ
አስገምጋሚው ድምፄ ፣ ጭጭ ብሎ ቀረ።
ሻል ያለኝ ሲመስለኝ
እንዲህም አስመኘኝ
ቃላት ከፊደላት ሰብስቤ
ሃሳብ ባ'ሳብ ላይ ደርቤ
አንደበቴ ተሞርዶ እንዳለቀ
ሃሳቤ ባ'ንዳፍታ ተፍረከረከ
ድንጋይ አንደመታው መስታወት ተሰነጠቀ።
በማዕበላማው የፍቅር ባህርሽ
ጀልባዬ ብትሰጥም አይግረምሽ
እንኳንስ የ'ኔ ኢምንት ጀልባ
ካንቺ ዉብ አይን ከቶ 'ማትገባ
ተወርዋሪው የፍቅርሽ ማዕበል
ግዙፉን መርከብም ያሰጥማል።
የፍቅርሽ ወጀብ ብርታቱ
ተተርኮ ላይዘለቅ ጥልቀቱ
ኮስማና ጀልባዬን አንስቶ
ካ'ለት ከቋጥኙ አጋጭቶ
ያረጀ አካላቷን ፈታትቶ
መደገፊያ ዘንጌን ነስቶ
አንደ'ዜ በፍቅርሽ ማዕበል ስደገፍ
ሌላ'ዜ በወጀቡ ተገፍቼ ስንሳፈፍ
ለይቼ ሳላውቅ ኩነቴን
መኖሬን ወይ አለመኖሬን
መሆኔን ቆሜ ሳበስር
አለመሆኔ ሲነቅለኝ ከሥር
በመኖሬ መኖር ሳጓራ
አለመኖሬ ገዝፎ ከጋራ
ወዲህ ረከስኩ ብዬ ስቆዝም
ወዲያ ዋጋዬ ንሮ ስደመም
ስሞት ስነሳ በፍቅር
ስለ ትንሣኤ መኖር
ከቶ እንዴት ብዬ ልጠራጠር?
ማክሰኞ 2 ሴፕቴምበር 2014
ዉዴ
አንቺን የሚመጥን ስጦታ ፍለጋ፣
ቁልቁለቱን ወረድሁ
አቀበቱን ወጣሁ
ወርቅ እንዳላመጣ፣
ከ'ግር እስከራስሽ እንድታጌጪበት
ካንቺ ወዲያ ላሳር ፣ በወርቅ አንጣሪነት
ጠጅ እንዳላመጣ
በአልማዝ ብርሌ ፣ ተቀድቶ 'ሚጠጣ
ካንቺ ወዲያ ጠጅ ጣይ
እንኩዋንስ ዘንድሮ ፣ ለርከርሞም አይታይ
ልቤን አንዳልሰጥሽ
የኔን ልብ የገራ ፣ አውራ ልብ የታደልሽ
ከሥጋ ነጥዬ ፣ ንፍሴን እንዳልቸርሽ
የኔ ብኩኗ ነፍስ ፣ ላንቺ 'ማትመጥንሽ
ያየሁት በሙሉ ካ'ይን 'ማይገባ ፣ የልብ 'ማያደርስ
ሆኖብኝ ልፋቴ ፣ ዉቅያኖስ በሲኒ ቀድቶ እንደመጨረስ
ቢጨንቀኝ ቢጠበኝ ፣ መስታወት ሰጠሁሽ
ራስሽን ስታዪ ፣ ድንገት ትዝ ብልሽ።
ቁልቁለቱን ወረድሁ
አቀበቱን ወጣሁ
ወርቅ እንዳላመጣ፣
ከ'ግር እስከራስሽ እንድታጌጪበት
ካንቺ ወዲያ ላሳር ፣ በወርቅ አንጣሪነት
ጠጅ እንዳላመጣ
በአልማዝ ብርሌ ፣ ተቀድቶ 'ሚጠጣ
ካንቺ ወዲያ ጠጅ ጣይ
እንኩዋንስ ዘንድሮ ፣ ለርከርሞም አይታይ
ልቤን አንዳልሰጥሽ
የኔን ልብ የገራ ፣ አውራ ልብ የታደልሽ
ከሥጋ ነጥዬ ፣ ንፍሴን እንዳልቸርሽ
የኔ ብኩኗ ነፍስ ፣ ላንቺ 'ማትመጥንሽ
ያየሁት በሙሉ ካ'ይን 'ማይገባ ፣ የልብ 'ማያደርስ
ሆኖብኝ ልፋቴ ፣ ዉቅያኖስ በሲኒ ቀድቶ እንደመጨረስ
ቢጨንቀኝ ቢጠበኝ ፣ መስታወት ሰጠሁሽ
ራስሽን ስታዪ ፣ ድንገት ትዝ ብልሽ።
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)