ሐሙስ 25 ሴፕቴምበር 2014

ማንም - ከየትም

 'ማልመደብ ከክርስቲያኑ ፣ ከሙስሊሙ ወይ ካ'ይሁዱ
'ማልፈረጅ ከቡድሃው ፣ ከሱፊው ፣ ከዜኑ ወይ ከሂንዱ
ከሃይማኖት ወይ ከባህል 'ማይመራኝ መንገዱ
ያልመጣሁ ከምሥራቁ ወይ ከምዕራቡ
ያ'ይደለሁ ከሰሜኑ ወይ ከደቡቡ
ያልፈለቅሁ ከባህሩ ፣ ከጥልቁ ከውቅያኖሱ
ያልወረድሁ ከደመናው ፣ ከሰማያዊ ክርታሱ
ከትቦ ያላስቀመጠኝ ፣ የፍጥረት ሀተታ ድርሳን
ዘሬ ግንዱ 'ማይመዘዝ ፣ ካ'ዳም እና ከሔዋን
ስፍራዬ ስፍራ የሌለዉ ሊጎበኘኝ ለሚተጋ
ዱካዬ ዱካው 'ማይገኝ የሚፈትን ለፍለጋ
መደብ ያልተበጀልኝ ከመንፈስ ወይ ከሥጋ
አይደለሁኝ ማንም
አይደለሁም የማንም
ከዚህኛዉ የለሁም
አልኖር ከሚመጣዉም
ያልመጣሁኝ ከየትም
የማልሄድ ወደ የትም
ማንም ነኝ ከየትም።

***********************
የ "Rumi"ን "Only Breath" የተሰኘዉን ግጥም አንብቤ ሳበቃ በ'ኔው ገልቱ ትርጉም ወደ አማርኛ የተቀየረ

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ