አንቺን የሚመጥን ስጦታ ፍለጋ፣
ቁልቁለቱን ወረድሁ
አቀበቱን ወጣሁ
ወርቅ እንዳላመጣ፣
ከ'ግር እስከራስሽ እንድታጌጪበት
ካንቺ ወዲያ ላሳር ፣ በወርቅ አንጣሪነት
ጠጅ እንዳላመጣ
በአልማዝ ብርሌ ፣ ተቀድቶ 'ሚጠጣ
ካንቺ ወዲያ ጠጅ ጣይ
እንኩዋንስ ዘንድሮ ፣ ለርከርሞም አይታይ
ልቤን አንዳልሰጥሽ
የኔን ልብ የገራ ፣ አውራ ልብ የታደልሽ
ከሥጋ ነጥዬ ፣ ንፍሴን እንዳልቸርሽ
የኔ ብኩኗ ነፍስ ፣ ላንቺ 'ማትመጥንሽ
ያየሁት በሙሉ ካ'ይን 'ማይገባ ፣ የልብ 'ማያደርስ
ሆኖብኝ ልፋቴ ፣ ዉቅያኖስ በሲኒ ቀድቶ እንደመጨረስ
ቢጨንቀኝ ቢጠበኝ ፣ መስታወት ሰጠሁሽ
ራስሽን ስታዪ ፣ ድንገት ትዝ ብልሽ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ