ሐሙስ 26 ዲሴምበር 2013

እድል

ሳማርር ከርሜ ፣ ዘመኔን በሙሉ
ጠማማ ነው ሲሉኝ ፣ ያርባ ቀን እድሉ

ለሌሎቹ ሲዘንብ ፣ ሁል ጊዜ
ለኔ አለማካፋቱ ፣ አንድም ጊዜ

ከትናንት ዛሬ ፣ መጣ ስል ከቤቴ
አልፎኝ እየሄደ ፣ ዕድል ጎረቤቴ

እሱስ ሁሌ ደጄ ፣ ይመላለስ ነበር
እኔ ባልሰራ እንጂ ፣ የሚንኳኳዉን በር።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ