ዓርብ 6 ዲሴምበር 2013

ማንዴላ

በአላማዉ ፍፁም ፀንቶ ፣
የዘር መድልዎን ያሸነፈ
ነገን ቀድሞ ተመልክቶ፣
ቂም በቀልን ያከሸፈ

ሰላማዊ ሽግግርን ፣
ተቀብሎ ያቀበለ
አሳዳጅ ጠላቶቹን ፣
ስለፍቅር ይቅር ያለ

ለብዙሃን ብርታት ሆኖ ፣
ለትግላቸው ማገር ባላ
ላመነበት ኖሮ ማለፍ ፣
እረፍቱ ነው ለማንዴላ::



 “When a man has done what he considers to be his duty to his people and his country, he can rest in peace.”  Nelson Mandela

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ