ማክሰኞ 3 ዲሴምበር 2013

በራስ መድመቅ

ካነበብከው አንድ መፅሐፍ ፣ እንቶ ፈንቶ እያቀለምክ
አገሬዉን አታደንቁር ፣ አዲስ ግኝት አንዳበሰርክ

ከህሊናህ ባህር ቀድተህ ፣ ያቀረብከው አዲስ ሃሳብ
ሳትኩለው ሳትቀባው ፣ ማብራቱ አይቀር እንደ ኮከብ

የሰው ወርቅ ተደግፈህ ፣ ባጉል ኩራት ከምትቀልጥ
የራስህን መዳብ ይዘህ ፣ ብትወድቅ እንኳ ተንፈራገጥ ::

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ