ማክሰኞ 3 ዲሴምበር 2013

ነፃነት በነፃ

ሳልፈን ሰጥተን  መስሎን የሚመለስ
የማሰብ ነፃነት ፣ እስኪቀረን ድረስ
አንኳንስ በአካል ፣ አይታይ በመንፈስ

አኛ ያቀድነዉን ፣ ሌላ እንዲሰራልን
ተቀምጠን ስንጠብቅ ፣ ነፃ የሚያወጣን
አዚህ ክፍት እስር ቤት ፣ አረጀን ሻገትን

ከፍርሃት እንቅልፍ ፣ በርግገን ከነቃን
እኔ ማለት ቀርቶ ፣ ለኛ ዘብ ከቆምን
ጎጠኝነት ሳይሆን ፣ ሰው መሆን ካስማማን
ከዛሬ አሻግረን ፣ ነገን ከተለምን
ለነፃነታችን ፣ እጅጉን ቅርብ ነን

ተምረን ከሆነ ካምናና ካቻምና
እርምጃችን ይሁን ፣ ሁሌም በጥሞና
ነፃነት በነፃ ፣ አይገኝምና

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ