ፍቅሬ ለኔ ምኔ?
ዘወትር ጠይቂያለሁ
በርካሽ መለኪያ ፣
ሁሌም መትሪያለሁ
ደም ግባት ቁመና ፣
ዳሌና ወዘና
በረዶ ጥርሶቿ ፣
ጨረቃ አይኖቿ
ጣቶቿ አለንጋ ፣
አፍንጫ ሰልካካ
ያ መቃው አንገቷ ፣
ያ ሳንቃው ደረቷ
ጀምሬ ከራስ ፀጉሯ ፣
ፈፅሜ በእግር ጥፍሯ
የሰውነት አካል ፣
ሳስቀምጥ ሳነሳ
ሳደንቅሽ ስክብሽ ፣
ጥያቄው ተረሳ።
በጥልቀት ሳስበው ፣
ያንቺን ትርጉም ለኔ
እጅግ ያንስብኛል ፣
ማለት ግማሽ ጎኔ
አካልሽ ቢያምርም ፣
ብዙም አልመሰጠኝ
አይንህ ላፈር ብለሽ ፣
ብትፈልጊ ሸኚኝ
አፈር ስገባልሽ ፣
ብቻ አንዴ ስሚኝ...
ያለሰበብ ያለምክንያት ፣
በሞኝነት የምወድሽ
አካልሽን ሸፍኖት ነው ፣
የማረከኝ ሰው-ነትሽ ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ