ረቡዕ 25 ዲሴምበር 2013

የማያውቁት ሀገር ናፍቆት

ከጎኔ ተቀምጦ ፣
ሳይተኛ እያለመ
አድማሱን ተሻግሮ ፣
እርቆ እየከተመ

ከምናቡ ጉዞ ፣
እመንገድ ጠብቄ
ወዴት ባሳብ ነጎድክ? ፣
ባነሳ ጥያቄ
     
እያሳበቀበት የፊቱ ገፅታ ፣  
በሚያልመው ሀገር ምች እንደተመታ 
'የማያውቁት ሀገር' ፣ 
'አይናፍቅም' ብሎ
መንጎዱን ቀጠለ ፣
ለመድረስ ቸኩሎ ። 

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ