ዓርብ 20 ዲሴምበር 2013

ጀግንነት

ሌሎችን ድል አርጎ ፣
'ጉሮ ወሸባዬ' የሚያዘፍን ጀግና
በእርግጥም ጎበዝ ነው ፣
ጠላትን ተጋፍጦ አንበርክኳልና
ግና በራሱ ላይ፣
ዘምቶ በፍም ወኔ
ራሱን አሸንፎ
ራሱን ሲማርክ ነው ፣
የምር ጀግና ለኔ ።


ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ