ስንፍናህ ተረስቶ ፣
ታታሪው ለፍቶአደር የምትባልበት
መሰሪነትህን ፣
በፍፁም ቅንነት የምትተካበት
ስስታምነትህ ፣
በልዩ ደግነት የሚለወጥበት
ወስላታነትህም ፣
በጨዋነት ታጥቦ ንፁህ'ምትሆንበት
ራስ ወዳድነትህ ፣
ለሌሎች በመኖር የሚዘከርበት
'ይድፋው!' ያለው ሁሉ ፣
'እኔ ልደፋለት' የሚያዜምበት
ቆሜ ታዘብኩልህ ፣
'ወዳጅ' ወገንህን የቀብርህ ዕለት::
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ