ሳማርር ከርሜ ፣ ዘመኔን በሙሉ
ጠማማ ነው ሲሉኝ ፣ ያርባ ቀን እድሉ
ለሌሎቹ ሲዘንብ ፣ ሁል ጊዜ
ለኔ አለማካፋቱ ፣ አንድም ጊዜ
ከትናንት ዛሬ ፣ መጣ ስል ከቤቴ
አልፎኝ እየሄደ ፣ ዕድል ጎረቤቴ
እሱስ ሁሌ ደጄ ፣ ይመላለስ ነበር
እኔ ባልሰራ እንጂ ፣ የሚንኳኳዉን በር።
ሐሙስ 26 ዲሴምበር 2013
ረቡዕ 25 ዲሴምበር 2013
የማያውቁት ሀገር ናፍቆት
ከጎኔ ተቀምጦ ፣
ሳይተኛ እያለመ
አድማሱን ተሻግሮ ፣
እርቆ እየከተመ
ከምናቡ ጉዞ ፣
እመንገድ ጠብቄ
ወዴት ባሳብ ነጎድክ? ፣
ባነሳ ጥያቄ
ሳይተኛ እያለመ
አድማሱን ተሻግሮ ፣
እርቆ እየከተመ
ከምናቡ ጉዞ ፣
እመንገድ ጠብቄ
ወዴት ባሳብ ነጎድክ? ፣
ባነሳ ጥያቄ
እያሳበቀበት የፊቱ ገፅታ ፣
በሚያልመው ሀገር ምች እንደተመታ
'የማያውቁት ሀገር' ፣
'አይናፍቅም' ብሎ
መንጎዱን ቀጠለ ፣
ለመድረስ ቸኩሎ ።
ዓርብ 20 ዲሴምበር 2013
ጀግንነት
ሌሎችን ድል አርጎ ፣
'ጉሮ ወሸባዬ' የሚያዘፍን ጀግና
በእርግጥም ጎበዝ ነው ፣
ጠላትን ተጋፍጦ አንበርክኳልና
ግና በራሱ ላይ፣
ዘምቶ በፍም ወኔ
ራሱን አሸንፎ
ራሱን ሲማርክ ነው ፣
የምር ጀግና ለኔ ።
'ጉሮ ወሸባዬ' የሚያዘፍን ጀግና
በእርግጥም ጎበዝ ነው ፣
ጠላትን ተጋፍጦ አንበርክኳልና
ግና በራሱ ላይ፣
ዘምቶ በፍም ወኔ
ራሱን አሸንፎ
ራሱን ሲማርክ ነው ፣
የምር ጀግና ለኔ ።
ሐሙስ 19 ዲሴምበር 2013
ሆድና ህሊና
የዛሬ ስንት ዓመት ፣ በነፃነት ማግስት
ህሊና ገጠመ ፣ ከሆዱ ጋር ሙግት
ከየጎራው ወጡ ፣ የፍትህ አማልክት።
ያልታወረ ህሊና ፣ ብሩህ ያገር ተስፋ
ሊቀጥል አላሻም ፣ወትሮ እንደተከፋ።
የሰላምን እሳት ፣ ላንቃዎች ለኮሱ
ብዕሮችም አልቀሩ ፣ እንደመነኮሱ።
የማይዝሉ አጆች ፣ የማይደክም አንደበት
ማን ሊመልሳቸው ፣ አብረው ባንድነት።
ህሊና ተርቦ ፣ ሆድ ከሚቀፈደድ
ባድር ባዮች ሴራ ፣ ሁሌ ከመሳደድ
ሳይሻል አይቀርም ፣ ጨርቅ ጥሎ ማበድ።
እብድስ ከለየለት ፣ ማንም ያዝንለታል
ጨርቁን እንኳን ቢጥል ፣ ዉራጅ ያለብሱታል
የሚበላው ቢያጣ ፣ ሰይጣን ያጎርሰዋል
አዉቆ አበድ መሆን ነው ፣ ከሁሉ 'ሚያስጠላ
እርባና የሌለው ፣ የሰው ቀጥፎ-በላ።
እብዶችም አይደሉ ፣ ወይ አውቆ አበዶች
ወገንም አይደሉ ፣ ወይ ጠላት መሳዮች
ከዚህ እየወሰዱ ፣ ከዚያ አቀባዮች
ከዚህ እየነቀሉ ፣ ከወዲያ ተካዮች
ከዚህ እያቦኩ ፣ ከዚያ ጋጋሪዎች
እዉነት ትፍረዳቸው ፣ እኚህን ጡት ነካሾች ።
ህሊና ገጠመ ፣ ከሆዱ ጋር ሙግት
ከየጎራው ወጡ ፣ የፍትህ አማልክት።
ያልታወረ ህሊና ፣ ብሩህ ያገር ተስፋ
ሊቀጥል አላሻም ፣ወትሮ እንደተከፋ።
የሰላምን እሳት ፣ ላንቃዎች ለኮሱ
ብዕሮችም አልቀሩ ፣ እንደመነኮሱ።
የማይዝሉ አጆች ፣ የማይደክም አንደበት
ማን ሊመልሳቸው ፣ አብረው ባንድነት።
ህሊና ተርቦ ፣ ሆድ ከሚቀፈደድ
ባድር ባዮች ሴራ ፣ ሁሌ ከመሳደድ
ሳይሻል አይቀርም ፣ ጨርቅ ጥሎ ማበድ።
እብድስ ከለየለት ፣ ማንም ያዝንለታል
ጨርቁን እንኳን ቢጥል ፣ ዉራጅ ያለብሱታል
የሚበላው ቢያጣ ፣ ሰይጣን ያጎርሰዋል
አዉቆ አበድ መሆን ነው ፣ ከሁሉ 'ሚያስጠላ
እርባና የሌለው ፣ የሰው ቀጥፎ-በላ።
እብዶችም አይደሉ ፣ ወይ አውቆ አበዶች
ወገንም አይደሉ ፣ ወይ ጠላት መሳዮች
ከዚህ እየወሰዱ ፣ ከዚያ አቀባዮች
ከዚህ እየነቀሉ ፣ ከወዲያ ተካዮች
ከዚህ እያቦኩ ፣ ከዚያ ጋጋሪዎች
እዉነት ትፍረዳቸው ፣ እኚህን ጡት ነካሾች ።
ማክሰኞ 17 ዲሴምበር 2013
እኔ ማነኝ?
የሰው ስህተት ለማመልከት፣
ከብርሃን ፈጥኜ የምከሰት
ጥያቄማ ተጠይቄ?
አላውቅምን የት አዉቄ
ግልፅነቴና ድፍረቴ፣
ወይ በብቅል ወይ በእብደቴ
ሲነሳ ጉድለት ድክመቴ፣
ላብ በላብ አጥንት ጅማቴ
እያረረ የቤቴ ድስት፣
የማማስል የጎረቤት
እኮ ታዲያ እኔ ማነኝ?
በመምሰል ያላወቃችሁኝ፣
ካንገት በላይ አታስቁኝ፣
እንቆቅልሼን መልሱልኝ፣
ካሰኛችሁም ሀገር ስጡኝ፣
እኔ ግን የናንተው ልጅ ነኝ።
ከብርሃን ፈጥኜ የምከሰት
ጥያቄማ ተጠይቄ?
አላውቅምን የት አዉቄ
ግልፅነቴና ድፍረቴ፣
ወይ በብቅል ወይ በእብደቴ
ሲነሳ ጉድለት ድክመቴ፣
ላብ በላብ አጥንት ጅማቴ
እያረረ የቤቴ ድስት፣
የማማስል የጎረቤት
እኮ ታዲያ እኔ ማነኝ?
በመምሰል ያላወቃችሁኝ፣
ካንገት በላይ አታስቁኝ፣
እንቆቅልሼን መልሱልኝ፣
ካሰኛችሁም ሀገር ስጡኝ፣
እኔ ግን የናንተው ልጅ ነኝ።
ሰኞ 16 ዲሴምበር 2013
ያለሰበብ የምወድሽ
ፍቅሬ ለኔ ምኔ?
ዘወትር ጠይቂያለሁ
በርካሽ መለኪያ ፣
ሁሌም መትሪያለሁ
ደም ግባት ቁመና ፣
ዳሌና ወዘና
በረዶ ጥርሶቿ ፣
ጨረቃ አይኖቿ
ጣቶቿ አለንጋ ፣
አፍንጫ ሰልካካ
ያ መቃው አንገቷ ፣
ያ ሳንቃው ደረቷ
ጀምሬ ከራስ ፀጉሯ ፣
ፈፅሜ በእግር ጥፍሯ
የሰውነት አካል ፣
ሳስቀምጥ ሳነሳ
ሳደንቅሽ ስክብሽ ፣
ጥያቄው ተረሳ።
በጥልቀት ሳስበው ፣
ያንቺን ትርጉም ለኔ
እጅግ ያንስብኛል ፣
ማለት ግማሽ ጎኔ
አካልሽ ቢያምርም ፣
ብዙም አልመሰጠኝ
አይንህ ላፈር ብለሽ ፣
ብትፈልጊ ሸኚኝ
አፈር ስገባልሽ ፣
ብቻ አንዴ ስሚኝ...
ያለሰበብ ያለምክንያት ፣
በሞኝነት የምወድሽ
አካልሽን ሸፍኖት ነው ፣
የማረከኝ ሰው-ነትሽ ።
ዘወትር ጠይቂያለሁ
በርካሽ መለኪያ ፣
ሁሌም መትሪያለሁ
ደም ግባት ቁመና ፣
ዳሌና ወዘና
በረዶ ጥርሶቿ ፣
ጨረቃ አይኖቿ
ጣቶቿ አለንጋ ፣
አፍንጫ ሰልካካ
ያ መቃው አንገቷ ፣
ያ ሳንቃው ደረቷ
ጀምሬ ከራስ ፀጉሯ ፣
ፈፅሜ በእግር ጥፍሯ
የሰውነት አካል ፣
ሳስቀምጥ ሳነሳ
ሳደንቅሽ ስክብሽ ፣
ጥያቄው ተረሳ።
በጥልቀት ሳስበው ፣
ያንቺን ትርጉም ለኔ
እጅግ ያንስብኛል ፣
ማለት ግማሽ ጎኔ
አካልሽ ቢያምርም ፣
ብዙም አልመሰጠኝ
አይንህ ላፈር ብለሽ ፣
ብትፈልጊ ሸኚኝ
አፈር ስገባልሽ ፣
ብቻ አንዴ ስሚኝ...
ያለሰበብ ያለምክንያት ፣
በሞኝነት የምወድሽ
አካልሽን ሸፍኖት ነው ፣
የማረከኝ ሰው-ነትሽ ።
ሐሙስ 12 ዲሴምበር 2013
ዓርብ 6 ዲሴምበር 2013
ማንዴላ
ሐሙስ 5 ዲሴምበር 2013
እኔ ልደፋለት
ስንፍናህ ተረስቶ ፣
ታታሪው ለፍቶአደር የምትባልበት
መሰሪነትህን ፣
በፍፁም ቅንነት የምትተካበት
ስስታምነትህ ፣
በልዩ ደግነት የሚለወጥበት
ወስላታነትህም ፣
በጨዋነት ታጥቦ ንፁህ'ምትሆንበት
ራስ ወዳድነትህ ፣
ለሌሎች በመኖር የሚዘከርበት
'ይድፋው!' ያለው ሁሉ ፣
'እኔ ልደፋለት' የሚያዜምበት
ቆሜ ታዘብኩልህ ፣
'ወዳጅ' ወገንህን የቀብርህ ዕለት::
ታታሪው ለፍቶአደር የምትባልበት
መሰሪነትህን ፣
በፍፁም ቅንነት የምትተካበት
ስስታምነትህ ፣
በልዩ ደግነት የሚለወጥበት
ወስላታነትህም ፣
በጨዋነት ታጥቦ ንፁህ'ምትሆንበት
ራስ ወዳድነትህ ፣
ለሌሎች በመኖር የሚዘከርበት
'ይድፋው!' ያለው ሁሉ ፣
'እኔ ልደፋለት' የሚያዜምበት
ቆሜ ታዘብኩልህ ፣
'ወዳጅ' ወገንህን የቀብርህ ዕለት::
ላቋራጭ ናፋቂው
ተቀምጠህ ሰማዩን ማውረድ ለሚቃጣህ
ወደ ስኬት በሊፍት መሄድ ለሚዳዳህ
በደረጃው ዉጣ እንዲያ ነው እሚያዋጣህ
ስትወጣ እርምጃህ ይከወን በጤና
እንዲያው አያድርገው አያምጣብህና
እንደመውጣት ሁሉ መውረድም አለና::
ወደ ስኬት በሊፍት መሄድ ለሚዳዳህ
በደረጃው ዉጣ እንዲያ ነው እሚያዋጣህ
ስትወጣ እርምጃህ ይከወን በጤና
እንዲያው አያድርገው አያምጣብህና
እንደመውጣት ሁሉ መውረድም አለና::
ማክሰኞ 3 ዲሴምበር 2013
በራስ መድመቅ
ካነበብከው አንድ መፅሐፍ ፣ እንቶ ፈንቶ እያቀለምክ
አገሬዉን አታደንቁር ፣ አዲስ ግኝት አንዳበሰርክ
ከህሊናህ ባህር ቀድተህ ፣ ያቀረብከው አዲስ ሃሳብ
ሳትኩለው ሳትቀባው ፣ ማብራቱ አይቀር እንደ ኮከብ
የሰው ወርቅ ተደግፈህ ፣ ባጉል ኩራት ከምትቀልጥ
የራስህን መዳብ ይዘህ ፣ ብትወድቅ እንኳ ተንፈራገጥ ::
አገሬዉን አታደንቁር ፣ አዲስ ግኝት አንዳበሰርክ
ከህሊናህ ባህር ቀድተህ ፣ ያቀረብከው አዲስ ሃሳብ
ሳትኩለው ሳትቀባው ፣ ማብራቱ አይቀር እንደ ኮከብ
የሰው ወርቅ ተደግፈህ ፣ ባጉል ኩራት ከምትቀልጥ
የራስህን መዳብ ይዘህ ፣ ብትወድቅ እንኳ ተንፈራገጥ ::
ነፃነት በነፃ
አሳልፈን ሰጥተን ፣ መስሎን የሚመለስ
የማሰብ ነፃነት ፣ እስኪቀረን ድረስ
አንኳንስ በአካል ፣ አይታይ በመንፈስ።
አኛ ያቀድነዉን ፣ ሌላ እንዲሰራልን
ተቀምጠን ስንጠብቅ ፣ ነፃ የሚያወጣን
አዚህ ክፍት እስር ቤት ፣ አረጀን ሻገትን።
ከፍርሃት እንቅልፍ ፣ በርግገን ከነቃን
እኔ ማለት ቀርቶ ፣ ለኛ ዘብ ከቆምን
ጎጠኝነት ሳይሆን ፣ ሰው መሆን ካስማማን
ከዛሬ አሻግረን ፣ ነገን ከተለምን
ለነፃነታችን ፣ እጅጉን ቅርብ ነን።
ተምረን ከሆነ፣ ካምናና ካቻምና
እርምጃችን ይሁን ፣ ሁሌም በጥሞና
ነፃነት በነፃ ፣ አይገኝምና።
የማሰብ ነፃነት ፣ እስኪቀረን ድረስ
አንኳንስ በአካል ፣ አይታይ በመንፈስ።
አኛ ያቀድነዉን ፣ ሌላ እንዲሰራልን
ተቀምጠን ስንጠብቅ ፣ ነፃ የሚያወጣን
አዚህ ክፍት እስር ቤት ፣ አረጀን ሻገትን።
ከፍርሃት እንቅልፍ ፣ በርግገን ከነቃን
እኔ ማለት ቀርቶ ፣ ለኛ ዘብ ከቆምን
ጎጠኝነት ሳይሆን ፣ ሰው መሆን ካስማማን
ከዛሬ አሻግረን ፣ ነገን ከተለምን
ለነፃነታችን ፣ እጅጉን ቅርብ ነን።
ተምረን ከሆነ፣ ካምናና ካቻምና
እርምጃችን ይሁን ፣ ሁሌም በጥሞና
ነፃነት በነፃ ፣ አይገኝምና።
ሰኞ 2 ዲሴምበር 2013
ትዉልድ
ያ ትዉልድ ሞቶ ፣ ተጋድሞ የቀረው
መግባባት ተስኖት ፣ ማስተዋል ርቆት ነው
ይህ ትዉልድ ራስ ወዳድ ፣ አስመሳይ የሆነው
የያ ትዉልድ ሴራ ፣ በቁሙ አጋድሞት ነው
የመጪዉን ትዉልድ ፣ ልዩ የሚያደርገው
ዉልደቱም እድገቱም ፣ ቅዥት መሆኑ ነው::
መግባባት ተስኖት ፣ ማስተዋል ርቆት ነው
ይህ ትዉልድ ራስ ወዳድ ፣ አስመሳይ የሆነው
የያ ትዉልድ ሴራ ፣ በቁሙ አጋድሞት ነው
የመጪዉን ትዉልድ ፣ ልዩ የሚያደርገው
ዉልደቱም እድገቱም ፣ ቅዥት መሆኑ ነው::
ዓርብ 29 ኖቬምበር 2013
ሀገሬ ወዴት ናት?
የሚያወጉባት ፣ ዜጎች በነፃነት፣
የሚነገርባት ፣ ከሐሰት ይልቅ እውነት፣
እኩል 'ሚታይባት ፣ ሁሉም ከሕግ ፊት፣
የሚከበርባት ፣ የዲሞክራሲ መብት፣
መንግስት በሃይማኖት ፣ እጅ የማይሰድባት፣
የዘራዉን ብቻ ፣ ሁሉም የሚያጭድባት፣
ሲኖሩባት እንጂ ፣ ኖሬ ያላየኋት፣
በናፍቆት ሰቀቀን ፣ አቅሌን ሳልስትባት፣
ሀገሬ ኢትዮጵያ ፣ ዉሰዱኝ ወዴት ናት?
የሚነገርባት ፣ ከሐሰት ይልቅ እውነት፣
እኩል 'ሚታይባት ፣ ሁሉም ከሕግ ፊት፣
የሚከበርባት ፣ የዲሞክራሲ መብት፣
መንግስት በሃይማኖት ፣ እጅ የማይሰድባት፣
የዘራዉን ብቻ ፣ ሁሉም የሚያጭድባት፣
ሲኖሩባት እንጂ ፣ ኖሬ ያላየኋት፣
በናፍቆት ሰቀቀን ፣ አቅሌን ሳልስትባት፣
ሀገሬ ኢትዮጵያ ፣ ዉሰዱኝ ወዴት ናት?
ሐሙስ 28 ኖቬምበር 2013
መስታወት ጓደኛ
በሸንጋይ ፈገግታ ፣
በሳቅ ጭስ የሚያጥነኝ
ሲቸግረው ብቻ ፣
ፈልጎ እሚያገኘኝ
እኔ ስፈልገው ፣
ደብዛው የሚርቀኝ
አንድም ቀን ድክመቴን ፣
ደፍሮ ያልነገረኝ
እንዲህ አይነትማ ፣
እልፍ ጓደኛ አለኝ
እኔን የናፈቀኝ ፣
አጅጉን የራበኝ
እንደመስታወቴ ፣
ብጉር ጠባሳዬን በግልፅ የሚያሳየኝ።
በሳቅ ጭስ የሚያጥነኝ
ሲቸግረው ብቻ ፣
ፈልጎ እሚያገኘኝ
እኔ ስፈልገው ፣
ደብዛው የሚርቀኝ
አንድም ቀን ድክመቴን ፣
ደፍሮ ያልነገረኝ
እንዲህ አይነትማ ፣
እልፍ ጓደኛ አለኝ
እኔን የናፈቀኝ ፣
አጅጉን የራበኝ
እንደመስታወቴ ፣
ብጉር ጠባሳዬን በግልፅ የሚያሳየኝ።
ረቡዕ 27 ኖቬምበር 2013
አስመሳይ አፍቃሪ
ወድሻለሁ ማለት፣
አርባ ክንድ የራቀው
ዉዱን በማራከስ፣
ቤት ዉስጥ የታወቀው
አይን ሲያርፍባት፣
በአይን ከምታውቀው
መውደዱን ይለብሳል፣
ቤት ደርሶ አስኪያወልቀዉ::
አርባ ክንድ የራቀው
ዉዱን በማራከስ፣
ቤት ዉስጥ የታወቀው
አይን ሲያርፍባት፣
በአይን ከምታውቀው
መውደዱን ይለብሳል፣
ቤት ደርሶ አስኪያወልቀዉ::
አስመሳይ ዲሞክራት
'እኔን ካልሰማችሁ' ፣
'ሰማይና ምድር ተከደነባችሁ'
እያለ እሚያሳቅቅ ፣
አዉራ አምባገነን መሆኑን አውቃችሁ
አደባባይ ወጥቶ ፣
'ካለኔ ዲሞክራት ላሳር ነው' ሲላችሁ
ለይምሰል አድናቆት ፣
እጅ ከነሳችሁ
ታዲያ አናንተ ከእርሱ ፣
በምን ተሻላችሁ?
'ሰማይና ምድር ተከደነባችሁ'
እያለ እሚያሳቅቅ ፣
አዉራ አምባገነን መሆኑን አውቃችሁ
አደባባይ ወጥቶ ፣
'ካለኔ ዲሞክራት ላሳር ነው' ሲላችሁ
ለይምሰል አድናቆት ፣
እጅ ከነሳችሁ
ታዲያ አናንተ ከእርሱ ፣
በምን ተሻላችሁ?
ማክሰኞ 26 ኖቬምበር 2013
ከተሸከማችሁን!
ነፃ አወጣናችሁ ፣ ካምባገነን ላንቃ
የድል ችቦ አብሩ ፣ ጭቆና አበቃ
ከዛሬ ጀምሮ ፣ ሕዝብ ነው አለቃ
በሕላችሁን ኑሩ ፣ ዳንኪራም ጨፍሩ
በማንነታችሁ ጭራሽ አንዳታፍሩ
ስም ስትጠየቁ ፣ ዘራችሁን ቁጠሩ
በጎጥ ወንዝ ገድበን ፣ የሸነሸናችሁ
በኛ ረቂቅ ጥበብ ፣ ከቶ እንዳይመስላችሁ
በዉሸት ስንሰብክ ፣ አሜን አያላችሁ
በቀደድነው ቦይ ዉስጥ ፣ እየፈሰሳችሁ
ጀርባችሁ ጠንካራ ፣ ወገባችሁ ምቹ
አኛን ለማስጋለብ ፣ ሰርክም አትሰለቹ
ፈቃዳችሁ ሆኖ ፣ ከተሸከማችሁን
መቁረጥ ተስኗችሁ ፣ ካደላደላችሁን
በልስልስ ጫንቃችሁ ፣ እንመቻቻለን
ታግሎ የሚያወርደን ፣ ካጣን ምን ጨነቀን!
የድል ችቦ አብሩ ፣ ጭቆና አበቃ
ከዛሬ ጀምሮ ፣ ሕዝብ ነው አለቃ
በሕላችሁን ኑሩ ፣ ዳንኪራም ጨፍሩ
በማንነታችሁ ጭራሽ አንዳታፍሩ
ስም ስትጠየቁ ፣ ዘራችሁን ቁጠሩ
በጎጥ ወንዝ ገድበን ፣ የሸነሸናችሁ
በኛ ረቂቅ ጥበብ ፣ ከቶ እንዳይመስላችሁ
በዉሸት ስንሰብክ ፣ አሜን አያላችሁ
በቀደድነው ቦይ ዉስጥ ፣ እየፈሰሳችሁ
ጀርባችሁ ጠንካራ ፣ ወገባችሁ ምቹ
አኛን ለማስጋለብ ፣ ሰርክም አትሰለቹ
ፈቃዳችሁ ሆኖ ፣ ከተሸከማችሁን
መቁረጥ ተስኗችሁ ፣ ካደላደላችሁን
በልስልስ ጫንቃችሁ ፣ እንመቻቻለን
ታግሎ የሚያወርደን ፣ ካጣን ምን ጨነቀን!
ሰኞ 25 ኖቬምበር 2013
ድንቄም ልሂቅ
ፊደል መቁጠር ከቶ ድንቁ
ማዕረግ ለሱ ቀለብ ስንቁ
የራስ ክብር እንቁ ወርቁ
አላውቅም ማለት ጭንቁ
መተባበር ለሱ ብርቁ
ባፉ ለወገን ተቆርቋሪ ፣
ዞር ብሎ ጉግጓድ ቆፋሪ
የወረቀት ላይ አንበሳ ፣
በብዕር ተከልሎ የሚያገሳ
እራሱ በፍርሃት ርዶ
በወገኑ ደምና አጥንት ፣
የለውጥ ጀምበር ይናፍቃል
እሱ ሰፊ አፉን ሊከፍት ፣
ሰፊዉን ህዝብ ይማግዳል።
ማዕረግ ለሱ ቀለብ ስንቁ
የራስ ክብር እንቁ ወርቁ
አላውቅም ማለት ጭንቁ
መተባበር ለሱ ብርቁ
ባፉ ለወገን ተቆርቋሪ ፣
ዞር ብሎ ጉግጓድ ቆፋሪ
የወረቀት ላይ አንበሳ ፣
በብዕር ተከልሎ የሚያገሳ
እራሱ በፍርሃት ርዶ
ምስኪን ወገኑን ማግዶ
በርግጎ ከሀገር ነጉዶበወገኑ ደምና አጥንት ፣
የለውጥ ጀምበር ይናፍቃል
እሱ ሰፊ አፉን ሊከፍት ፣
ሰፊዉን ህዝብ ይማግዳል።
የበይ ተመልካች
ያ የጥንቱ አርበኛ ፣ ደሙን ያፈሰሰዉ
የሀገርን ድንበር ፣ አስከብሮ ያለፈው
ቀና ብሎ ቢያየን ፣ ምንኛ በቆጨው
የበይ ተመልካች ፣ ሆነን ሲታዘበዉ።
የሀገርን ድንበር ፣ አስከብሮ ያለፈው
ቀና ብሎ ቢያየን ፣ ምንኛ በቆጨው
የበይ ተመልካች ፣ ሆነን ሲታዘበዉ።
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)