ተደግፋ ባጥንት
ተመርጋ በሥጋ
ተለስና በደም፣
እንቡጦቿን ቀጥፋ
ክፉ ዘመን አልፋ
ደብዛዋ ቢጠፋ፣
በየአደባባዩ ስፈልግ ስማስን
በደግ ሲነሳ ባጣው ሃያል ስሟን፣
በጨለመ ተስፋ ጥጋ-ጥጉን ሳስስ
እግር ጣለኝና ከምታቃስት ነፍስ፣
ደሟንም ተመጣ
ሥጋዋን ተግጣ
ተሰብሮ አጥንቷ
መቅኔዋ ሲጠጣ፣
ባህያ ቆዳ ላይ ተንጋላ ተኝታ
አየኋት ሀገሬን በቀን ጅብ ተበልታ።
እሑድ 30 ማርች 2014
ሐሙስ 27 ማርች 2014
ያልዘራዉን ሊያጭድ
ጀግንነት ፣ ግብረገብ ፣ ሀገር ወዳድነት
ከዝና ባሻገር ፣ ለእሴት ኗሪነት
እብስ አሉ ጠፉ ፣ ተነኑ ባንድነት
ወኔ አልባ ሆኖ ፣ የቆረጠ ተስፋ
ሃሞቱ የፈሰሰ ፣ የተኛ ያንቀላፋ
ይለናል ያ ትውልድ
ያልዘራዉን ሊያጭድ።
በነፈዝነቱ ፣ እንዲህ እሚደቆሰው
ይህ የተኛ ትውልድ ፣ ማንስ ቀሰቀሰው?
ማንስ ምርኩዝ ሆኖ ፣ ማንስ ተነስ አለው?
ማንስ ከመማረር ፣ ማምረርን አሳየው?
ማንስ ከመልፈስፈስ ፣ ብርታት አስታጠቀው?
ማንስ የማይነትብ ፣ ፍሬ-ነገር ፃፈ?
ማንስ ሕያው ሥራ ፣ ትቶለት አለፈ?
በትናንት ልኬት እየተሰፈረ
'ሁሉም ድሮ ቀረ' እየተዘመረ
ያኔ ያልተዘራው ፣ ዛሬ ላይታጨድ
ላልሰመረው ሁሉ ፣ ይታማል ይህ ትውልድ።
ከዝና ባሻገር ፣ ለእሴት ኗሪነት
እብስ አሉ ጠፉ ፣ ተነኑ ባንድነት
ወኔ አልባ ሆኖ ፣ የቆረጠ ተስፋ
ሃሞቱ የፈሰሰ ፣ የተኛ ያንቀላፋ
ይለናል ያ ትውልድ
ያልዘራዉን ሊያጭድ።
በነፈዝነቱ ፣ እንዲህ እሚደቆሰው
ይህ የተኛ ትውልድ ፣ ማንስ ቀሰቀሰው?
ማንስ ምርኩዝ ሆኖ ፣ ማንስ ተነስ አለው?
ማንስ ከመማረር ፣ ማምረርን አሳየው?
ማንስ ከመልፈስፈስ ፣ ብርታት አስታጠቀው?
ማንስ የማይነትብ ፣ ፍሬ-ነገር ፃፈ?
ማንስ ሕያው ሥራ ፣ ትቶለት አለፈ?
በትናንት ልኬት እየተሰፈረ
'ሁሉም ድሮ ቀረ' እየተዘመረ
ያኔ ያልተዘራው ፣ ዛሬ ላይታጨድ
ላልሰመረው ሁሉ ፣ ይታማል ይህ ትውልድ።
እርቅ
ለይምሰል ለታይታ
ስትለኝ ይቅርታ ፣
ሳይፈልቅ ከስሜትህ
ከልብህ ከውስጥህ ፣
ቂም ቋጥሮ ህሊናህ
ቢጨብጠኝ እጅህ ፣
ብትስመኝ ብታቅፈኝ
ያዞ እንባ እያነባህ፣
ከውስጥህ ተኳርፈህ ፣ ከኔ ከመታረቅ
መጀመሪያ ነገር ፣ አንተ ካንተ ታረቅ።
ዓርብ 21 ማርች 2014
በእርግጥ ጎድተኸኛል
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
በናፍቆት ሰቀቀን
በመገፋት ቆፈን
እንደማለዳ ዉርጭ አኮራምተኸኛል።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
ዱካህን አጥፍተህ በፈለግኩህ ጊዜ
ሰው አልባ አርገኸኝ ባገሬ በወንዜ
እንደቆላ ሃሩር አጠውልገኸኛል።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
ሆነክ ያልሆንከዉን
ኖሮክ የሌለህን
ስትቃዥ በቁምህ
ክፉ ህልሜ ሆነህ እንቅልፌን ነጥቀሃል።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
ዳብሰህ ሌላ ገላ
ጎርሰህ ሌላ ከንፈር
በቅናት ማዕበል አናውጠህ አዳፍተህ
ከሰው ተራ አውጥተህ
ከመሃል ዳር ገፍተህ
ከንፈሬን በጥርሴ አስነክሰኸኛል።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
እቶን ወላፈኑ በሚንቦገቦገው
በበደል ምጣድ ላይ አገላብጠኸኛል
አሻሮ እስኪወጣኝ እስካ'ር ቆልተኸኛል ።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
ዉስጤ ግን ይልሃል......
ከበደል ከስቃይ ከበቀል ባሻገር
እጅ ባፍ እሚያስጭን የረቀቀ ሚስጥር
በልብ የሚዳሰስ ከስሜት ጥላ ስር
ማሪው ማሪው ይላል እውነተኛ ፍቅር።
በናፍቆት ሰቀቀን
በመገፋት ቆፈን
እንደማለዳ ዉርጭ አኮራምተኸኛል።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
ዱካህን አጥፍተህ በፈለግኩህ ጊዜ
ሰው አልባ አርገኸኝ ባገሬ በወንዜ
እንደቆላ ሃሩር አጠውልገኸኛል።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
ሆነክ ያልሆንከዉን
ኖሮክ የሌለህን
ስትቃዥ በቁምህ
ክፉ ህልሜ ሆነህ እንቅልፌን ነጥቀሃል።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
ዳብሰህ ሌላ ገላ
ጎርሰህ ሌላ ከንፈር
በቅናት ማዕበል አናውጠህ አዳፍተህ
ከሰው ተራ አውጥተህ
ከመሃል ዳር ገፍተህ
ከንፈሬን በጥርሴ አስነክሰኸኛል።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
እቶን ወላፈኑ በሚንቦገቦገው
በበደል ምጣድ ላይ አገላብጠኸኛል
አሻሮ እስኪወጣኝ እስካ'ር ቆልተኸኛል ።
በእርግጥ ጎድተኸኛል፣
ዉስጤ ግን ይልሃል......
ከበደል ከስቃይ ከበቀል ባሻገር
እጅ ባፍ እሚያስጭን የረቀቀ ሚስጥር
በልብ የሚዳሰስ ከስሜት ጥላ ስር
ማሪው ማሪው ይላል እውነተኛ ፍቅር።
ረቡዕ 19 ማርች 2014
ባህር ላይ ስራመድ
ዋናተኛው መንጋ
ሲንሳፈፍ ከታች ላይ፣
እኔ ግን ብቸኛው
ስራመድ ባህሩ ላይ፣
ለዚህ አይነት ጥበብ
አልደረሰም ብለው፣
ያዩትን ጥሬ ሀቅ
ወደጎን ትተው፣
ከቁብም ሳይቆጥሩኝ
አለፉኝ ናቅ አርገው።
እኔ ግን ብቸኛው
በሰፊው ባህር ላይ፣
ሲሻኝ ተቀምጬ
ኑሮን ሳሰላስል፣
ሲለኝ ተነስቼ
ስራመድ ያለእክል፣
ዋናተኛው መንጋ
ሰማሁት እንዲህ ሲል፣
"በዚህ በባህር ላይ ቆሞ 'ሚራመደው
እንደኛ ተንሳፎ መዋኘት ከብዶት ነው"።
ሲንሳፈፍ ከታች ላይ፣
እኔ ግን ብቸኛው
ስራመድ ባህሩ ላይ፣
ለዚህ አይነት ጥበብ
አልደረሰም ብለው፣
ያዩትን ጥሬ ሀቅ
ወደጎን ትተው፣
ከቁብም ሳይቆጥሩኝ
አለፉኝ ናቅ አርገው።
እኔ ግን ብቸኛው
በሰፊው ባህር ላይ፣
ሲሻኝ ተቀምጬ
ኑሮን ሳሰላስል፣
ሲለኝ ተነስቼ
ስራመድ ያለእክል፣
ዋናተኛው መንጋ
ሰማሁት እንዲህ ሲል፣
"በዚህ በባህር ላይ ቆሞ 'ሚራመደው
እንደኛ ተንሳፎ መዋኘት ከብዶት ነው"።
ማክሰኞ 18 ማርች 2014
ባለጊዜ ታሪክ ጣፊ
የራሱን አሻራ ለማኖር ሲሳነው
የታሪክ ድሪቶ ሲጥፍ የሚዉለው
ባለ-ጊዜው ብእሩ ሀቅ እየደለዘ
የቆረቆረዉን ወቅጦ እየደቆሰ
የዛሬን መሰረት ትናንትን ናደና
መንደርኛ ጀብዱ አንቆ ጋተኝና
ያን የጋራ ቁስል
ያን የጋራ ገድል
ያን የጋራ ጀግና
በሰፈር ጉድጓድ ዉስጥ በጠበጠውና
ታሪክን አቡክቶ ጋገረበት መ'ና።
የታሪክ ድሪቶ ሲጥፍ የሚዉለው
ባለ-ጊዜው ብእሩ ሀቅ እየደለዘ
የቆረቆረዉን ወቅጦ እየደቆሰ
የዛሬን መሰረት ትናንትን ናደና
መንደርኛ ጀብዱ አንቆ ጋተኝና
ያን የጋራ ቁስል
ያን የጋራ ገድል
ያን የጋራ ጀግና
በሰፈር ጉድጓድ ዉስጥ በጠበጠውና
ታሪክን አቡክቶ ጋገረበት መ'ና።
ሰኞ 17 ማርች 2014
መኖር
መኖር፣
ያለፈውን ፅልመት፣
ማህደሩን ዘግቶ።
መኖር፣
ባለው በቀረው ላይ፣
የተስፋ ዘር ዘርቶ።
መኖር፣
ከፊት ለሚመጣው፣
ቅን ልቦናን ከፍቶ።
አለበለዚያማ.......
ነገር-አለሙን ካከረርነው'ማ
ብንወጣት ብንወርዳት፣
ይህቺን ረቂቅ ዓለም
የጀመራት - ሁሉም፣
የጨረሳት - ማንም!
ያለፈውን ፅልመት፣
ማህደሩን ዘግቶ።
መኖር፣
ባለው በቀረው ላይ፣
የተስፋ ዘር ዘርቶ።
መኖር፣
ከፊት ለሚመጣው፣
ቅን ልቦናን ከፍቶ።
አለበለዚያማ.......
ነገር-አለሙን ካከረርነው'ማ
ብንወጣት ብንወርዳት፣
ይህቺን ረቂቅ ዓለም
የጀመራት - ሁሉም፣
የጨረሳት - ማንም!
እሑድ 16 ማርች 2014
ሰው ለሰው
ለሰው መድሃኒቱ
ሰው ነው ቢሉኝ ጊዜ
ህመሜን ባዋየው
ቁስሌን ባሳየው
በፈውስ አስመስሎ ፣ ሸፍጥ ሰደደና
ስቃዬን አባሰው ፣ አስመረቀዘና።
......................እናም ተረዳሁኝ
የማዳኑን ያክል ፣ መድሃኒት በመሆን
ለሰው በሽታዉም ፣ ራሱ ሰው አንደሆን።
ሰው ነው ቢሉኝ ጊዜ
ህመሜን ባዋየው
ቁስሌን ባሳየው
በፈውስ አስመስሎ ፣ ሸፍጥ ሰደደና
ስቃዬን አባሰው ፣ አስመረቀዘና።
......................እናም ተረዳሁኝ
የማዳኑን ያክል ፣ መድሃኒት በመሆን
ለሰው በሽታዉም ፣ ራሱ ሰው አንደሆን።
ረቡዕ 12 ማርች 2014
ያላወቅከው
እንደንጋት ጮራ፣
ከሚያበራው ፈገግታዬ
እንደበረዶ ነጥቶ፣
ከሚያስካካው ጥርሴ
እቅፍ ሳም አርገኝ፣
ከሚለው ገላዬ
.
.
.
ከዚህ ሁሉ ጀርባ መሽጎ
አንተን 'ሚታዘብህ ተሸሽጎ
የዋህነትህን 'ሚያይ አጮልቆ
እድሜ ዘመንህን ብትሰጠው
ተመራምረህ 'ማትጨብጠው
በልቤ ጓዳ የቋጠርኩት
አለ ያልገባህ ጠጣር እውነት
ስውር የታሪክ ጉንጉን ስፌት።
ከሚያበራው ፈገግታዬ
እንደበረዶ ነጥቶ፣
ከሚያስካካው ጥርሴ
እቅፍ ሳም አርገኝ፣
ከሚለው ገላዬ
.
.
.
ከዚህ ሁሉ ጀርባ መሽጎ
አንተን 'ሚታዘብህ ተሸሽጎ
የዋህነትህን 'ሚያይ አጮልቆ
እድሜ ዘመንህን ብትሰጠው
ተመራምረህ 'ማትጨብጠው
በልቤ ጓዳ የቋጠርኩት
አለ ያልገባህ ጠጣር እውነት
ስውር የታሪክ ጉንጉን ስፌት።
ወሊድ-አልባ ምጥ
መክኗል እንዳይባል ፣
የብሶት ምርጥ ዘር ፣ የኋሊት አዳቅሎ
በሕሊናው ማህፀን፣ ይዟል አንጠልጥሎ።
ጨንግፏል እንዳንል፣
ሌት ተቀን በማማጥ ፣ ሲቀመጥ ሲነሳ
ጭቆና ያጎበጠው ፣ አንድ ወገቡ ሳሳ።
አዋላጁም ሆኖ ፣ የሌለው እርባና
ምጡም ወሊድ-አልባ ፣ አስጨናቂ ሆነና
ሽሉን ተሸክመን ፣ ነግቶ እየጠባ
የሚወለደውን ፣ ስንጠብቅ ባበባ
አፈር ላይ ያለነው አፈር እንዳንገባ።
የብሶት ምርጥ ዘር ፣ የኋሊት አዳቅሎ
በሕሊናው ማህፀን፣ ይዟል አንጠልጥሎ።
ጨንግፏል እንዳንል፣
ሌት ተቀን በማማጥ ፣ ሲቀመጥ ሲነሳ
ጭቆና ያጎበጠው ፣ አንድ ወገቡ ሳሳ።
አዋላጁም ሆኖ ፣ የሌለው እርባና
ምጡም ወሊድ-አልባ ፣ አስጨናቂ ሆነና
ሽሉን ተሸክመን ፣ ነግቶ እየጠባ
የሚወለደውን ፣ ስንጠብቅ ባበባ
አፈር ላይ ያለነው አፈር እንዳንገባ።
ሰኞ 10 ማርች 2014
ቅዳሜ 8 ማርች 2014
ዉሻና ሰው
ሰውና ዉሻማ ፣ ምን አንድ አድርጓቸው
ለሰው የማይዋጥ ፣ ልዩነት አላቸው።
የተራበ ዉሻ ፣ የጠገበ ለታ
ተመልሶ አይነክስም ፣ ያበላዉን ጌታ
የተራበ ሰው ግን ፣
የቀረበለትን ፣ አንድ ሁለቴ ጎርሶ
ደረቅ ጎሮሮውን ፣ በምፅዋት አርሶ
ጠኔ ያደከማት ፣ ነፍሱ መለስ ስትል
ይጎነጉነዋል ፣ የተንኮሉን ፈትል።
ለሰው የማይዋጥ ፣ ልዩነት አላቸው።
የተራበ ዉሻ ፣ የጠገበ ለታ
ተመልሶ አይነክስም ፣ ያበላዉን ጌታ
የተራበ ሰው ግን ፣
የቀረበለትን ፣ አንድ ሁለቴ ጎርሶ
ደረቅ ጎሮሮውን ፣ በምፅዋት አርሶ
ጠኔ ያደከማት ፣ ነፍሱ መለስ ስትል
ይጎነጉነዋል ፣ የተንኮሉን ፈትል።
የስሜቴ አንባቢ
አንቺ የኔ አካል ፣ ሳትኖሪ ከጎኔ
መሰንበት ነው እንጂ ፣ መኖር አይደል የኔ
ከኔ ሐሴት ይልቅ ፣ ያንቺን እርካታ ላይ
አድማሱን አቋርጠሽ ፣ በሞቴ ቶሎ ነይ።
"ወድሻለሁ" ቃሉ ፣ ምን ቢቀጭጭብኝ
ሳስቶ ሰዋ-ሰዉ ፣ ቅኔው ቢሰልብኝ
እንደበጋ ጅረት ፣ ቃላት ቢደርቁብኝ
እንደበቴ እንደሃረግ ፣ ቢጠላለፍብኝ
አንቺ ስላለሽኝ ፣ ብቻ እድለኛ ነኝ።
ለምን ቢባል ደግሞ ....................
ገፀ-ማንነቴን ፣ ግልጥልጥ አድርገሽ
የዉስጤን አስተዋይ ፣ አንባቢዬ አንቺ ነሽ።
ቅዳሜ 1 ማርች 2014
ሕይወት ማለት ወዳጄ
ሕይወት ማለት ፣
ሕይወት እኮ ሙዚቃ ናት ፣
በረቂቅ ቅኝት የምታዜማት
በዉብ ቅላፄ የምታስጌጣት ፣
ጉዳት ሲጨብጥህ ትተክዝባት ፣
ፍርሃት ሲከጅልህ ትፎክርባት ፣
ፌሽታ ሲነሽጥህ ትፈነጥዝባት።
አየህ ወዳጄ ፣
ሕይወት ማለት፣
ሕይወት እኮ ዉድድር ናት ፣
ህሊና በሚባል የራስ ዳኛ፣
በሕግጋት የምትመራ
መሸነፍ የሚሉት ፅልመት ፣
ማሸነፍ የሚባል ንጋት ፣
በፈረቃ የሚያደምቋት
ወጪ ወራጁን እምታሳይ ፣
የፍትጊያ አውድማ ናት።
እና ወዳጄ ፣
ሕይወት ማለት ፣
ሕይወት እኮ መስዋዕትነት ናት ፣
እንዳሻህ በብላሽ ፣ ከየትም የማታፍሳት
ወገብህን ሸብ ጠበቅ አርገህ ፣
ጥፍርህ አስኪቆስል ዳገት ቧጠህ ፣
ወደ ማምሻው ነው የምትቆናጠጣት።
ስማኝማ ወዳጄ ፣
ሕይወት ማለት ፣
ሕይወት እኮ ቅኔ ናት ፣
ያለ ጠብ-መንጃ ዘርፈህ ፣
በቀለጠው ሰሟ ተውልዉለህ ፣
በነጠረው ወርቋ ትደምቅባት።
ከምንም በላይ ወዳጄ ፣
ሕይወት ማለት ፣
ሕይወት እኮ ፍቅር ናት ፣
በቁሳቁስ ቅራቅንቦ ፣ በንዋይ የማትለካት ፣
ሳትሰጥ ተቀብለህ ፣ ሳትቀበል የምትሰጣት።
(የበድሉ ዋቅጅራን "ሀገር ማለት የኔ ልጅ" በማሰብ የተፃፈ)
ሕይወት እኮ ሙዚቃ ናት ፣
በረቂቅ ቅኝት የምታዜማት
በዉብ ቅላፄ የምታስጌጣት ፣
ጉዳት ሲጨብጥህ ትተክዝባት ፣
ፍርሃት ሲከጅልህ ትፎክርባት ፣
ፌሽታ ሲነሽጥህ ትፈነጥዝባት።
አየህ ወዳጄ ፣
ሕይወት ማለት፣
ሕይወት እኮ ዉድድር ናት ፣
ህሊና በሚባል የራስ ዳኛ፣
በሕግጋት የምትመራ
መሸነፍ የሚሉት ፅልመት ፣
ማሸነፍ የሚባል ንጋት ፣
በፈረቃ የሚያደምቋት
ወጪ ወራጁን እምታሳይ ፣
የፍትጊያ አውድማ ናት።
እና ወዳጄ ፣
ሕይወት ማለት ፣
ሕይወት እኮ መስዋዕትነት ናት ፣
እንዳሻህ በብላሽ ፣ ከየትም የማታፍሳት
ወገብህን ሸብ ጠበቅ አርገህ ፣
ጥፍርህ አስኪቆስል ዳገት ቧጠህ ፣
ወደ ማምሻው ነው የምትቆናጠጣት።
ስማኝማ ወዳጄ ፣
ሕይወት ማለት ፣
ሕይወት እኮ ቅኔ ናት ፣
ያለ ጠብ-መንጃ ዘርፈህ ፣
በቀለጠው ሰሟ ተውልዉለህ ፣
በነጠረው ወርቋ ትደምቅባት።
ከምንም በላይ ወዳጄ ፣
ሕይወት ማለት ፣
ሕይወት እኮ ፍቅር ናት ፣
በቁሳቁስ ቅራቅንቦ ፣ በንዋይ የማትለካት ፣
ሳትሰጥ ተቀብለህ ፣ ሳትቀበል የምትሰጣት።
(የበድሉ ዋቅጅራን "ሀገር ማለት የኔ ልጅ" በማሰብ የተፃፈ)
ደንበኛ ይሁኑ ለ፡
ልጥፎች (Atom)