ረቡዕ 12 ማርች 2014

ያላወቅከው

እንደንጋት ጮራ፣
ከሚያበራው ፈገግታዬ
እንደበረዶ ነጥቶ፣
ከሚያስካካው ጥርሴ
እቅፍ ሳም አርገኝ፣
ከሚለው ገላዬ
.
.
.
ከዚህ ሁሉ ጀርባ መሽጎ
አንተን 'ሚታዘብህ ተሸሽጎ
የዋህነትህን 'ሚያይ አጮልቆ

እድሜ ዘመንህን ብትሰጠው
ተመራምረህ 'ማትጨብጠው
በልቤ ጓዳ የቋጠርኩት
አለ ያልገባህ ጠጣር እውነት
ስውር የታሪክ ጉንጉን ስፌት።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ