ሐሙስ 27 ማርች 2014

እርቅ

ለይምሰል ለታይታ 
ስትለኝ ይቅርታ ፣ 
ሳይፈልቅ ከስሜትህ 
ከልብህ  ከውስጥህ ፣
ቂም ቋጥሮ ህሊናህ 
ቢጨብጠኝ እጅህ ፣ 
ብትስመኝ ብታቅፈኝ 
ያዞ እንባ እያነባህ፣ 
ከውስጥህ ተኳርፈህ ፣ ከኔ ከመታረቅ 
መጀመሪያ ነገር ፣ አንተ ካንተ ታረቅ።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ