ቅዳሜ 8 ማርች 2014

የስሜቴ አንባቢ


አንቺ የኔ አካል ፣ ሳትኖሪ ከጎኔ
መሰንበት ነው እንጂ ፣ መኖር አይደል የኔ
ከኔ ሐሴት ይልቅ ፣ ያንቺን እርካታ ላይ
አድማሱን አቋርጠሽ ፣ በሞቴ ቶሎ ነይ።

"ወድሻለሁ" ቃሉ ፣ ምን  ቢቀጭጭብኝ
ሳስቶ ሰዋ-ሰዉ ፣ ቅኔው ቢሰልብኝ
እንደበጋ ጅረት ፣ ቃላት ቢደርቁብኝ
እንደበቴ እንደሃረግ ፣ ቢጠላለፍብኝ
አንቺ ስላለሽኝ ፣ ብቻ እድለኛ ነኝ።

ለምን ቢባል ደግሞ ....................

ገፀ-ማንነቴን ፣ ግልጥልጥ አድርገሽ
የዉስጤን አስተዋይ ፣ አንባቢዬ አንቺ ነሽ።

3 አስተያየቶች: