ጀግንነት ፣ ግብረገብ ፣ ሀገር ወዳድነት
ከዝና ባሻገር ፣ ለእሴት ኗሪነት
እብስ አሉ ጠፉ ፣ ተነኑ ባንድነት
ወኔ አልባ ሆኖ ፣ የቆረጠ ተስፋ
ሃሞቱ የፈሰሰ ፣ የተኛ ያንቀላፋ
ይለናል ያ ትውልድ
ያልዘራዉን ሊያጭድ።
በነፈዝነቱ ፣ እንዲህ እሚደቆሰው
ይህ የተኛ ትውልድ ፣ ማንስ ቀሰቀሰው?
ማንስ ምርኩዝ ሆኖ ፣ ማንስ ተነስ አለው?
ማንስ ከመማረር ፣ ማምረርን አሳየው?
ማንስ ከመልፈስፈስ ፣ ብርታት አስታጠቀው?
ማንስ የማይነትብ ፣ ፍሬ-ነገር ፃፈ?
ማንስ ሕያው ሥራ ፣ ትቶለት አለፈ?
በትናንት ልኬት እየተሰፈረ
'ሁሉም ድሮ ቀረ' እየተዘመረ
ያኔ ያልተዘራው ፣ ዛሬ ላይታጨድ
ላልሰመረው ሁሉ ፣ ይታማል ይህ ትውልድ።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ