ማክሰኞ 18 ማርች 2014

ባለጊዜ ታሪክ ጣፊ

የራሱን አሻራ ለማኖር ሲሳነው
የታሪክ ድሪቶ ሲጥፍ የሚዉለው
ባለ-ጊዜው ብእሩ ሀቅ እየደለዘ
የቆረቆረዉን ወቅጦ እየደቆሰ
የዛሬን መሰረት ትናንትን ናደና
መንደርኛ ጀብዱ አንቆ ጋተኝና
ያን የጋራ ቁስል
ያን የጋራ ገድል
ያን የጋራ ጀግና
በሰፈር ጉድጓድ ዉስጥ በጠበጠውና
ታሪክን አቡክቶ ጋገረበት መ'ና።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ