ዋናተኛው መንጋ
ሲንሳፈፍ ከታች ላይ፣
እኔ ግን ብቸኛው
ስራመድ ባህሩ ላይ፣
ለዚህ አይነት ጥበብ
አልደረሰም ብለው፣
ያዩትን ጥሬ ሀቅ
ወደጎን ትተው፣
ከቁብም ሳይቆጥሩኝ
አለፉኝ ናቅ አርገው።
እኔ ግን ብቸኛው
በሰፊው ባህር ላይ፣
ሲሻኝ ተቀምጬ
ኑሮን ሳሰላስል፣
ሲለኝ ተነስቼ
ስራመድ ያለእክል፣
ዋናተኛው መንጋ
ሰማሁት እንዲህ ሲል፣
"በዚህ በባህር ላይ ቆሞ 'ሚራመደው
እንደኛ ተንሳፎ መዋኘት ከብዶት ነው"።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ