በምናብ መገለጥ ተጋግሮ
በብርሃን ሰይፍ ካልተቆረሰ፣
በፅናት መቀነት ጠብቆ
ባንጀት ካንጀት ካልተቋጠረ፣
በመራር ያሞት ከረጢት
በእውነት ካልተሰተረ፣
በሃሳብ እንዝርት ሹሮ
በስሜት ቀመር ተዳውሮ
በተቡ ቃላት ካልተሸመነ፣
በዉበት ጥለት ተቋጭቶ
በሕብረ-ቀለም ካልተሸለመ...
ካንገት በላይ ተጠምቆ
ቅራሪ ስንኝ ቢቀዳም፣
ምላስን ከማራስ አልፎ
የግጥምን ጥም አይቆርጥም።
ምንም አስተያየቶች የሉም:
አስተያየት ይለጥፉ