ረቡዕ 9 ኤፕሪል 2014

ይመስገነው አለን

ይመስገነው አለን ፣
ቁጥርን እንደ ቁርጥ
ቆርጠን እየበላን፣

ይመስገነው አለን ፣
እምባን እንደ አምቦውሃ
ቀድተን እየጠጣን፣

ይመስገነው አለን ፣
ጨለማ እንደ ፋኖስ
ዞትር እያበራን፣

ይመስገነው አለን ፣
ቁጭት እንደ ባቡር
ተሳፍረን ሽው እያልን፣

ይመስገነው አለን ፣
እጅግ እንደረቅቀን
እንደተንደላቀቅን
እየሌለን አለን።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ