ማክሰኞ 1 ኤፕሪል 2014

እነርሱ ለእርሱ

ያረገዝውን እያማጡ
ያማጠውን እየወለዱ
የወለደውን እየሳሙ
ያሳደገውን እየዳሩ
የሞተበትን እየቀበሩ
ሙት-አመት እየዘከሩ
በምስለ-እርሱ ሲኖሩ፣
እርሱ ሲፈልግ እርሱን
ስጋው ቢሸኛት ነፍሱን፣
ያልሆናቸው ግን የሆኑት
ጨክነው ሜዳ ላይ ሳይጥሉት፣
በእልፍ ፍራንክ በተገዛ
በተሰራ ከርጥብ ዋንዛ
በልኩ ጎጆ ቀለሱና
ያፈር ካባ ደረቡና
አስሸለቡት ላይል ቀና።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ