ማክሰኞ 29 ኤፕሪል 2014

ሰሚ ማጣት

አንገቴ አይል ቀና ፣ እንዳምናው ዘንድሮ፤
በደም መጣጭ ተባይ ፣ ጫንቃዬ ተወሮ።
ከላዬ አሽቀንጥሬ ፣ አላፈርጠው ነገር፤
እጄ ተጠፍሯል ፣ ግራው ከቀኙ ጋር።
እንዳልደባልቀው ፣ መንደሩን በሩምታ፤
ልጉሙ ልሳኔ ፣ ነጥፏል ለኡኡታ።
የጆሮ ኩሊ እንጂ ፣ ሰሚ በሌለበት፤
በግፍ አዳራሽ ዉስጥ ፣ ጥግ ይዤ በትዝብት፤
በዝምታዬ ፍም ፣ አቀልጣለሁ ጩኸት።

ምንም አስተያየቶች የሉም:

አስተያየት ይለጥፉ